የቼልሲ የሽያጭ ጉዳይ እልባት አግኝቷል።
▪️የሎስአንጀለስ ዶጀርስ ፣ ሌከርስ እና ስፓርክስ በከፊል ባለቤት የሆኑት ቶድ ቦይሌ 5.3 ቢሊዮን ዶላር በማውጣት ቼልሲን መግዛታቸው የሚታወስ ሲሆን የወረቀት ስራዎች ባለማለቃቸው የእንግሊዝ መንግስት የቼልሲ እገዳን ሙሉ-ለሙሉ አላነሳም ነበር። አሁን ግን ጉዳዩ እልባት በማግኘት ቶድ ቦይሌ የቼልሲን ክለብ ግዢ ጉዳይ ሙሉ ለሙሉ በእንግሊዝ መንግስት ተቀባይነት አግኝቷል።
▪️ቶማስ ቱኸልም ለቀጣይ የውድድር ዘመን የተከላካይ መስመራቸውን ማጠናከር አላማቸው እንደሚሆን ያስታወቁ ሲሆን ለዚህም ከአዲሱ ባለሀብት እስከ 200 ሚሊዮን ፓውንድ በጀት እንደተመደበላቸው እየተገለፀ ይገኛል።
▪️አንቶኒዮ ሩዲገር ወደ ሪያል ማድሪድ ፣ ሴሳር አዝፕሊኬታ እንዲሁም ማርኮስ አሎንሶም ወደ ባርሴሎና ለማቅናት መውጫው በር እንደተጠጉ ተነግሯል።እነሱን ለመተካት ካሳለፍነው ክረምት አንስቶ ሲከታተሉት የነበረው እና እቅዳቸው የሆነውን የ23 አመቱ ፈረንሳዊ ኢንተርናሽናል ጁሊስ ኩንዴን ወደ ስታም ፎርድ ብሪጅ ማምጣት ተቀዳሚ አላማቸው እንደሚሆን ዘ ቴሌግራፍ ዘግቧል።
▪️ ከሱ በተጨማሪ የ20 አመቱ ክሮሺያዊ ግራቪዶል በአውሮፓ ውስጥ ድንቅ እንቅስቃሴ እያሳዩ ከሚገኙ ተከላካዮች መካከል የሚጠቀስ ነው።ይህን የግራ መስመር ተከላካይ እንዲሁም በማንቸስተር ዩናይትድ በጥብቅ የሚፈለገውን ስፔናዊ ፓው ቶሬስ እንዲሁም የአትሌቲኮ ማድሪዱን ተከላካይ ሆዜ ማሪያ ሄሜኔዝን ለማስፈረም ከክለቦቻቸው ጋር ንግግር መጀመራቸው ታውቋል።
ሚካኤል ደጀኔ።