ከ20 አመት በታች የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን የሆነው ክለብ ታውቋል።

▪️የ2014 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ በወላይታ ድቻ አሸናፊነት ሲጠናቀቅ ሀዋሳ ከተማ እና አርባምንጭ ከተማ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቅ ችለዋል።

በሁለት ምድብ ተከፍሎ ሲካሄድ የቆየው የ2014 የውድድር ዓመት የዙር ውድድር ባለፈው ሳምንት የምድብ ሀ በወላይታ ድቻ ፣ የምድብ ለ በሀዋሳ ከተማ አሸናፊነት መጠናቀቁ የሚታወስ ሲሆን የውድድሩን አጠቃላይ አሸናፊ ለመለየት ዛሬ የፍፃሜ ጨዋታ ተከናውኖ ወላይታ ድቻ ተጋጣሚው ሀዋሳ ከተማን 2-0 በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት መሆን ችሏል።

▪️የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ፣ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን እንዲሁም የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ አሊሚራ መሀመድ በክብር እንግድነት ተገኝተው ጨዋታውን የተከታተሉ ሲሆን ከዋንጫ ጨዋታው አስቀድሞ ሶስተኛ ደረጃን ለመያዝ ከየምድባቸው ሁለተኛ ሆነው ያጠናቀቁት አርባምንጭ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ጨዋታቸውን አካሂደዋል። አርባምንጭ ከተማ 1-0 በሆነ ጠባብ ውጤት በማሸነፍ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁን አረጋግጧል።

በዚህም መሰረት ለአርባምንጭ ከተማ የነሀስ ሜዳሊያ ፣ ለሀዋሳ ከተማ የብር እንዲሁም ለአሸናፊው ወላይታ ዲቻ የወርቅ ሜዳሊያ ተበርክቶለታል። ፋሲል ከተማ በበኩሉ የፀባይ (የስፖርታዊ ጨዋነት) ዋንጫ ተበርክቶለታል።

ሚካኤል ደጀኔ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.