የሊቨርፑል የክረምቱ የመጀመሪያ ፈራሚ።
▪️የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል በቀጣይ አመት የአጥቂ መስመሩን ይበልጥ ለማጠናከር ደፋ ቀና እያለ ይገኛል። የክረምቱ የመጀመሪያ ፈራሚያቸውንም አግኝተዋል። የ19 አመቱን ፋቢዮ ካርቫልሆን ዘንድሮ ፕሪሚየር ሊጉን ዳግም ከተቀላቀለው ከፉልሀም በቋሚነት አዘዋውረውታል።
▪️ዘንድሮ ፉልሀም ወደ ፕሪሚየር ሊጉ እንዲያድግ ቁልፍ ሚና ከተጫወቱ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ሲሆን ባደረጋቸው 36 ጨዋታዎች 10 ጎሎች ሲያስቆጥር 8 ኳሶች አመቻችቶ ማቀበልም ችሏል። ሊቨርፑል ለዚህ ተጫዋች 8 ሚሊዮን ፓውንድ እንደሚከፍልም ገተገልጿል። በየርገን ክሎፕ ስር እምቅ ብቃቱን በማሳየት የቀጣይ የውድድር ዘመን ድምቀት ይሆናል ተብሎም ተገምቷል።
ሚካኤል ደጀኔ።