ባለቀ ሰአት ዋጋ የከፈለው ወልቂጤ ከተማ።

25ኛ ሳምንቱ ላይ የሚገኘው የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በባህርዳር ስቴዲየም መካሄዱን ቀጥሏል።

በምሳ ሰአቱ (7:00) መርሀ-ግብር

▪️ሀዲያ  ሆሳዕና 1-1 ወልቂጤ ከተማ
90+3’⚽️ተስፋዬ አለባቸው       18′ ጌታነህ ከበደ

▪️የመጀመሪያው አጋማሽ ግብ አስቅጥረው ሲመሩ የነበሩት ወልቂጤዎች በሁለተኛው አጋማሽ መጠናቀቂያ ደቂቃዎች ላይ በተከላካዮች የትኩረት ማነስ ምክንያት ነጥብ ተጋርተው ወተዋል።

▪️ለወልቂጤ ከተማ 1 ጎል ያስቆጠረው ጌታነህ ከበደ የውድድር ዘመኑ 13ኛ ግቡ ሆኖ ተመዝግቧል። የኮኮብ ግብ አግቢነት ፉክክሩንም ከሲዳማ ቡናው አጥቂ ይገዙ ቦጋለ ጋር መስተካከል ችሏል።

▪️ውጤቱን ተከትሎ ሀድያ ሆሳዕና በ33 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ

▪️ወልቂጤ ከተማ በበኩሉ በ30 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል

ከጨዋታው በኋላ ሁለቱም አሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

▪️የወልቂጤ ከተማ አሰልጣኝ ተመስገን ዳና 🗣 ጥሩ እንቅስቃሴ አድርገናል። ቀድመን ጎል አስቆጥረን ውጤቱን ለማስጠበቅ ጥረት አድርገናል ግን ባለቀ ሰአት ግብ አስተናግደናል።ስለ ዳኝነት ብዙ ማውራት አይጠበቅብኝም እነሱ ስራቸውን ይፈትሹ እኛም ስራችንን እንፈትሻለን ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።

▪️ የሀድያ ሆሳዕና አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት በበኩሉ 🗣 የመጀመሪያው አጋማሽ ጥሩ ነበርን ማለት አልችልም። ነጥቡ ለሁለታችንም አስፈላጊ ስለነበር ፉክክር ነበረው። ሁለተኛው አጋማሽ ላይ ያደረግነው ጥረት ፍሬ አፍርቶ ነጥብ መውሰድ ችለናል። ብለዋል

▪️ሊጉ ከአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ሲመለስ ሀድያ ሆሳዕና ከ ጅማ አባ ጅፋር እንዲሁም ወልቂጤ ከተማ ከ መከላከያ የሚገናኙ ይሆናል።

ሚካኤል ደጀኔ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.