የሴቶች የሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ።

በሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ በጁቬንትስ አሊያንዝ ስቴዲየም ተካሂዷል።

▪️ባርሴሎና 1-3 ሊዮን
41’⚽️ ፑቴላስ         6’⚽️ ሄንሪ
                  23’⚽️ ሄገር በርግ
                  33’⚽️  ማካሪዮ

▪️ዘንድሮ ለ21ኛ ጊዜ ስሙን ቀይሮ የሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ መባል ከጀመረ ደግሞ ለ13ኛ ጊዜ የተካሄደው የሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ በፈረንሳዩ ክለብ ሊዮን አሸናፊነት ተጠናቋል።

▪️የአምና ሻምፒዮኖቹ የባርሴሎና ሴቶች ቡድን በላሊጋው 1 ጨዋታ ሳይሸኘፉ ካደረጉት 30 ጨዋታዎች 90 ነጥብ በማሳካት አይበገሬነታቸውን ስላሳዩ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን የማንሳት ግድመ-ግምት አጥኝተው ነበር።

▪️የባርሴሎና ሴቶች ቡድን የአምና ሻምፒዮን እንደመሆናቸው መጠን በተከታታይ ዋንጫውን ከፍ ለማድረግ የሊዮን ሴቶች ቡድን በበኩሉ በውድድሩ ያላቸውን ስም ለማስጠበቅ ብርቱ ፉክክር አድርገዋል።

▪️ሊዮን ጨዋታውን  ለ8ኛ ጊዜ ይህን ውድድር ማሳካት ችለዋል።

ሚካኤል ደጀኔ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.