አነጋጋሪው የኪሊያን ምባፔ የዝውውር ድራማ በስተመጨረሻ እልባት አግኝቷል።

▪️ኪሊያን ምባፔ ይፋዊ በሆነ መልኩ በውድድር ዘመኑ የመጨረሻ ጨዋታ ፒ ኤስ ጂ በሜዳው ፓርክ ዴ ፕሪንስ ከ ሜትስ በሚያደርጉት መርሀ-ግብር ላይ ለደጋፊዎቹ ውል ማራዘሙን ይፋ አድርጓል። ጨዋታውንም 5-0 ያሸነፉ ሲሆን ኪሊያን ምባፔ ሀትሪክ መስራት ችሏል።

▪️ምባፔም ሀሳቡን እንዲ ሲል አስቀምጧል። 🗣 ” እዚ ክለብ ውስጥ የእግር ኳስ ህይወቴን ለመቀጠል በመወሰኔ ደስተኛ ነኝ። ሁሌም እንደምለው ነው ለኔ ፓሪስ ቤቴ ነው ፣ ከተማዬም ነው። ዋንጫዎችን ከዚ ቡድን ጋር ለማሳካት ዝግጁ ነኝ” ብሏል።

▪️ውሉንም እስከ 2025 ሰኔ ወር ድረስ ማራዘሙ ይፋ ሲሆን የክለቡ ፕሬዚዳንት ናስር አል ካሊፋ በበኩሉ “ይህ በክለቡ ታሪክ ትልቅ ምዕራፍ ነው። ለክለቡ የወደፊት እቅድ እና አቅጣጫ ላይ የራሱን ሚና ሜዳ ላይ እና ከሜዳ ውጪ ይጫወታል። ዛሬ በጣም ደስ ብሎኛል ፣ ኮርቻለሁም ዛሬ በክለባችን ቆንጆ ገፆ ፆፈናል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

▪️ኪሊያን ምባፔ ራሱ ለሪያል ማድሪድ አለቃ ፊዮሬንቲኖ ፔሬዝ በመደወል ከአክብሮት ጋር ማድሪድ ያቀረበለትን ውል መቀበል እንደማይችል ገልፆላቸዋል።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.