የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ ሶስት ዳኞች ላይ የቅጣት ውሳኔ አስተላለፏል።
▪️የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 24ኛ ሳምንት በተደረጉ ስምንት ጨዋታዎች 12 በጨዋታ 3 በፍጹም ቅጣት ምት በድምሩ 15 ጎሎች ሲቆጠሩ 49 ቢጫ ካርድ እና አንድ ቀይ ካርድ በተጫዋቾችና የቡድን አመራሮች ላይ ተመዟል።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ውጤት ማጽደቅና የጨዋታ ታዛቢዎች ሪፖርት ለማየት በትናንትናው እለት ባደረገው ስብሰባ ከዳኝነት አንፃር ክስ የቀረበባቸውን ጉዳዮች ለብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ ለውሳኔ አስተላልፏል።
▪️በሳምንቱ ከተደረጉ ጨዋታዎች ወላይታ ድቻን ከ ሲዳማ ቡና ያጫወቱት ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ለሚ ንጉሴ እና ረዳት ዳኛ አብዱ ይጥና ውጤት የሚያስቀይር ስህተት መስራታቸው እንዲሁም ሀድያ ሆሳዕናን ከኢትዮጵያ ቡና ያጫወተው ዋና ዳኛ ሚኬሌ ጠዓመ ተጫዋችን አፀያፊ ስድብ ስለመሳደቡ ሪፖርት ከመደረጉ በተጨማሪም ለየጨዋታዎቹ በወላይታ ድቻ እና ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የቴክኒክ ክስ ቀርቦባቸዋል።
▪️የኢትዮጵያ ብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴም ሶስቱን ዳኞች ለጊዜው ውድድሩ ከሚካሄድበት ባህር ዳር ከተማ ወደ መጡበት ከተማ እንዲመለሱ ውሳኔ ያስተላለፈ ሲሆን ቀጣይ ውሳኔዎችንም በሂደት እንደሚገልፅ ለኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርና ስነ ስርዓት ኮሚቴ አሳውቋል።
ሚካኤል ደጀኔ።