አፄዎቹ ድል ቀንቷቸዋል።

የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 24ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በባህርዳር ስቴዲየም መካሄዳቸውን ቀጥለዋል።

▪️በእለቱ ሁለተኛ ጨዋታ ወይም በ(7 ሰአቱ) መርሀ-ግብር።

▪️መከላከያ 1-2 ፋሲል ከተማ
5’⚽️ አሚን ነስሩ (ፍ.ቅ.ም)  11’⚽️ ሽመክት ጉግሳ
                      74’⚽️ ናትናኤል ገ/ጊዮርጊስ

▪️በተከታታይ የሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ላይ ነጥብ እየወሰደ መነቃቃት ላይ የሚገኘውን መከላከያ እና ከመሪው ቅ/ጊዮርጊስ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ለሚጥበብ ከሚጥረውን ፋሲል ከተማ ያገናኘው የምሳ ሰአቱ መርሀ-ግብር በፋሲል ከተማ አሸናፊነት ተጠናቋል።

▪️መከላከያ ከተከታታይ ድሎች በኋላ ማለትም ከቅ/ጊዮርጊስ ጋር ነጥብ ከተጋራ በኋላ ኢትዮጵያ ቡናን ፣ ሀድያ ሆሳዕናን እንዲሁም ሲዳማ ቡናን አሸንፎ በ24ኛው ሳምንት በፋሲል ከነማ ተሸንፏል።

▪️ባሳለፍነው ሳምንት ከባህርዳር ከተማ ጋር ተቀይረው ገብተው ውጤት ያስገኙት ናትናኤል እና አጥቂው ፍፁም በ በረከት እና ኦኪኪ አፎላቢ በመተካት በ59 ደቂቃ መግባታቸው አሁንም ለውጤቱ ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል።

▪️አሰልጣኝ ሀይሉ ነጋሽ ባልተለመደ መልኩ ሙጅብ ቃሲምን በቀድሞ ቦታው ማለትም በተከላካይ ቦታ ላይ ከ ከድር ኩሊባሊ ጋር አጣምረውታል።

▪️ውጤቱን ተከትሎ ፋሲል ከተማ በ46 ነጥብ ከመሪው ቅ/ጊዮርጊስ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 8 ሲያጠብ መከላከያ በበኩሉ በ30 ነጥብ ባለበት 8ኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ተገዷል።

▪️ከጨዋታው በኋላ የሁለቱም ቡድኖች አሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

▪️የፋሲል ከተማ አሰልጣኝ ሀይሉ ነጋሽ 🗣 እያንዳንዱ ጨዋታ ለኛ ከባድ ነው። ግን ድል ቀንቶናል። ሙጅብ ቃሲም ከዚ በፊት የነበረበት ቦታ ስለሆነ ብዙም አልከበደውም በሚገባ ተወጥቶታል። ተጫዋቾች በቅጣት እና በጉዳት ስላጣን አማራጭ ስላልነበረን ነው እሱን በተከላካይ ቦታ ለማጫወት የተገደድነው። ለቀጣይ ለምናደርገው ጨዋታም ለሁሉም ቡድኖች እንደምንዘጋጀው ተዘጋጅተን ውጤት ይዘን ለመውጣት ወደሜዳ  እንገባለን።

▪️የመከላከያ ም/አሰልጣኝ ዮርዳኖስ አባይ በበኩሉ 🗣 በተጫዋቾቼ እንቅስቃሴ እጅግ በጣም ደስተኛ ነኝ። ወጤት ባይቀናንም ማለት ነው። በቀጣይ ከዚ ደግሞ የተሻለ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ ብዬ እጠብቃለሁ።

▪️በቀጣይ ወይም በ25ኛ ሳምንቱ መርሀ-ግብር ፋሲል ከተማ ከ መሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ከወዲሁ የሚጠበቅ ሲሆን መከላከያ በበኩሉ ከ ድሬዳዋ ከተማ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።
     
  ሚካኤል ደጀኔ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.