የጣናው ሞገድ ድል ቀንቶታል።

24ኛው ሳምንት ላይ የደረሰው የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በባህርዳር ስቴዲየም መካሄዳቸውን ቀጥለዋል።

በ7 ሰአቱ መርሀ-ግብር።

▪️ባህር ዳር ከተማ 1-0 አዳማ ከተማ
5’⚽️ ተመስገን ደረሰ

▪️ ውጤቱን ተከትሎ ባህርዳር ከተማ በ29 ነጥብ 9ኛ ደረጃን ለጊዜውም ቢሆን ከ ወልቂጤ ከተማ መረከብ ችሏል። ባህርዳር ከተማ በሜዳው የመጀመሪያውን 3 ነጥብ ማሳካት ችሏል።

▪️የውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው አዳማ ከተማ በያዘው 27 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

▪️ከጨዋታው በኋላ የሁለቱም ቡድን አሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

▪️የባህርዳር ከተማው አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሀም መብራቱ 🗣 በፈለኩት መንገድ ጨዋታው ሄዷል ማለት ባልችልም። ግን በጊዘረ ያስቆጠርነውን ኳስ አስጠብቆ ለመውጣት ያደረጉት ጥረት በጣም አደንቃለሁ ፣ በቀጣይ ላለብ ጨዋታ ስህተቶቻችንን አርመን ማጥቃት ላይ የተመሰረተ እንቅስቃሴ ይዘን እንቀርባለን። ደጋፊዎቻችንም እንዲሁ ቡድናችንን የጀርባ አጥንት ናቸው ለውጤታችን ብቻ ሳይሆን ለምናደርገው እንቅስቃሴ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ ስለዚህ እነሱንም በጣም ማመስገን አሰፈልጋለሁ ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

▪️ የአዳማ ከተማው ፋሲል ተካልኝ በበኩሉ 🗣 ሁለተኛው አጋማሽ ትንሽ ውጥረት የበዛበት ነበር ፣ የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ በፈለግነው መሰረት ነው ጨዋታውን የጀመርነው እድሎችን ፈጥረናል ግን መጠቀም አልቻልንም።ሳይታሰብ ወደ ወራጅ ቀጠናዎቹ እየተጠጋን ነው ፣ በደንብ መስራት ይጠበቅብናል።

▪️ በቀጣይ ማለተሰም በ25ኛው ሳምንት ባህርዳር ከተማ ከ ሲዳማ ቡና እንዲሁም አዳማ ከተማ ከ ሰበታ ከተማ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

ሚካኤል ደጀኔ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.