የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ድራማ እንደቀጠለ ነው።

ሳውዝሀምፕተን 1-2 ሊቨርፑል
13’⚽️ ሬድመንድ     27’⚽️ ሚናሚኖ
                               57’⚽️ ማቲፕ

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 37ኛ ሳምንት ጨዋታ በሴንትሜሪ ስቴዲየም ሳውዛምፕተን ማንቸስተር ሲቲ ላይ ጫና ለመፍጠር አስበው የመጡትን ሊቨርፑሎች አስተናግደዋል። አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ከ ኤፍ ኤ ካፑ ጨዋታ 9 ተጫዋቾችን ቀይሮ ነበር ወደ ሜዳ የገባው።

▪️ጨዋታው ከተጀመረ በ13 ደቂቃ ግን ከጎል የራቀው እንግሊዛዊው ናታን ሬድመንድ የመታው ኳስ አሊሰን ቤከር መረብ ላይ አርፋ ሳውዛምፕተን ቀዳሚ መሆን ቻሉ። ናታን ሬድመንድ ከ14 ወር በኋላ ነው ኳስን ከመረብ ያዋሀደው።

▪️ መሪነታቸው ግን ለ14 ደቂቃ ብቻ ነው የቆየው። እ.ኤ.አ በ2020 ታህሳስ ወር አንስቶ በፕሪሚየር ሊጉ ለሊቨርፑል መሰለፍ ያልቻለው ጃፓናዊው ታኩሚ ሚናሚኖ አምና ግማሽ የውድድር ዘመኑን በውሰት ያሳለፈበት ሳውዛምፕተን ላይ የአቻነቷን ጎል አስገኝቷል። ደስታውንም ከመግለፆ ተቆጥቧል።

▪️የመጀመሪያው አጋማሽም 1 አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል። በሁለተኛው አጋማሽ ሊቨርፑል አምበሉ ጆርዳን ሄንደርሰንን በተጎዳው ጆ ጎሜዝ ተተክቶ ወደ ሜዳ ገብቷል። ሊቨርፑሎች በተደጋጋሚ  እድሎችን ለመፍጠር ጥረት ሲያደርግ ቆይቶ በ57 ደቂቃ የተገኘውን የማዕዘንጨምት ተከላካዩ ጆኤል ማቲፕ ቡድኑ መምራት ያስቻለች ግብ አስቆጥሯል።የውድድር ዘመኑ ሶስተኛ ጎሉም ሆኖ ተመዝግቧል።

▪️መደበኛው የጨዋታ እንቅስቃሴ በዚሁ ውጤት የተጠናቀቀ ሲሆን ሊቨርፑል ነጥቡን 89 በማድረስ ማንቸስተር ሲቲ ላይ ጫናውን ያሳደረበትን ውጤት አስመዝግቧል።

▪️የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በቀጣይ ሳምንት የሚጠናቀቅ ሲሆን የዋንጫው ባለቤት ማን ይሆናል የሚለው ጥያቄ በስፖርት ቤተሰቡ ከወዲሁ ተጠባቂ ሆኗል። በ38ኛው ሳምንትመርሀ-ግብር በተመሳሳይ ሰአት ላይ ማንቸስተር ሲቲ በሜዳው ኤቲሀድ ስቴዲየም አስቶንቪላን ሲያስተናግድ ሊቨርፑል በሜዳው አንፊልድ ዎልቭስን ያስተናግዳል።

ሚካኤል ደጀኔ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.