3ኛ ደረጃን የመያዝ እድሉን ያመከነው ኢትዮጵያ ቡና።
የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 24ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በባህርዳር ስቴዲየም መካሄዳቸውን ጀምረዋል።
▪️ሀድያ ሆሳዕና 1-0 ኢትዮጵያ ቡና
22’⚽️ ሳምሶን ጥላሁን( ፍ/ምት)
▪️ሀድያ ሆሳእና ከ 3 ተከታታይ ሽንፈት በኋላ ወደ ድል የተመለሰበትን ውጤት ሲያስመዘግብ የውድድር ዘመኑ 8ኛ ድል አስመዝግቧል። ኢትዮጵያ ቡና በበኩሉ ከ 3 ተከታታይ ድል በኋላ ሽንፈትን አስተናግዷል። የውድድር ዘመኑ ደግሞ 8ኛ ሽንፈት ሆኖ ተመዝግቧል።
▪️63ኛው ደቂቃ ላይ የቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና የፊት መስመር ተጫዋች ሀብታሙ ታደሰ የኢትዮጵያ ቡና ግብ ጠባቂ በረከት አማረ ጥፋት ተጠቅሞ ያስቆጠራትን ግብ የእለቱ የመሀል ዳኛ ሚካኤል ጣዕመ በእጅ ተነክቷል በሚል የሻሩበት አጋጣሚ የጨዋታው አነጋጋሪ ጉዳይ ነው።
▪️ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና በ34 ነጥብ 6ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ
▪️ሀድያ ሆሳዕና በበኩኑ ነጥቡን 32 በማድረስ ደረጃውን ወደ 7ኛ ከፍ ማድረግ ይችላል።
▪️ከጨዋታው በኋላ የሁለቱም ቡድኖች አሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
▪️የሀድያ ሆሳዕናው ሙሉጌታ ምህረት 🗣 ባህርዳር ከመጣን ምንም ድል አልቀናንም ስለዚህ ከዚህ መንፈስ ለመውጣት ነጥቡ ያስፈልገን ነበር እሱን አሳክተናል። ምንም ክፍተት አልሰጠናቸውም ለጨዋታው ተዘጋጅተን ነበር የመጣነው ጎልም አላስተናገድንም ይህ ደግሞ ለቀጣይ ጨዋታዎቻችንም ስነ-ልቦናችንን ሚያነቃቃ ጥሩ ስንቅ ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
▪️የኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ በበኩሉ🗣 ከሜዳችን ወጥተን እነሱ ሜዳ ላይ መንቀሳቀስ አልከበደንም ግን ያሰብነውን ማሳካት አልቻልንም። የእለቱ ዋና ዳኛ ሲሳደብ በጆሮዬ ሰምቼዋለሁ ይህ ስፖርታዊ ጨዋነት አይመስለኝም። ተጫዋች ከሰደበው በካርድ መቅጣት እንጂ መመላለስ ከዳኛ የሚጠበቅ አይመስለኝም እንዲሁም የመጀመሪያው ጎል ላይም የመስመር ዳኛው ስህተት እንደሰሩ ጠቁመዋል።
▪️በቀጣይ ሀድያ ሆሳዕና ከ ወልቂጤ ከተማ እንዲሁም ኢትዮጵያ ቡና ከ ሀዋሳ ከተማ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።
ሚካኤል ደጀኔ።