ፓውሎ ዲባላ አሊያንዝን ዛሬ ይሰናበታል።
▪️ ፓውሎ ዲባላ ዛሬ የሚያደርገው ጨዋታ በ ጁቬንትስ ማልያ የመጨረሻው እንደሚሆን እና ክለቡንም እንደሚለቅ አስታውቋል።
▪️የ28 አመቱ ፓውሎ ዲባላ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ስሙ ከተለያዩ ክለቦች ጋር እየተነሳ ይገኛል። ኢንተርሚላን ፣ ሊቨርፑል ፣ አርሰናል ይጠቀሳሉ።
▪️ይህ አርጀንቲናዊ በ2015 ፓሌርሞን ለቆ ጁቬንቱስን ከለቀቀ በኋላ 5 ተከታታይ የጣልያን ሴሪያ(ስኩዴቶ) ከፍ አድርጎ ያነሳው የአሮጊቷ ስብስብ ቁልፍ አባል መሆኑ ይታወቃል። ይህ አጥቂ 4 ጊዜ የኮፓ ኢታሊያ ዋንጫንም ከቡድኑ ጋር አሳክቷል። በ2017 የሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታም ተጫውቷል ዋንጫውን ማሳካት ባይችልም ማለት ነው። በቀጣይ ሳምንት ወደ ፍራንቺ አርቴሚዮ ስቴዲየም አቅንቶ ፊዮሬንቲናን ከማግኘቱ በፊት ዛሬ ላዚዮን በሜዳቸው አሊያንዝ ስቴዲየም ክለቡን የሚሰናበት ይሆናል።
▪️በማህበራዊ ትስስር ገፁ ፓውሎ ዲባላ “የመሰናበቻ ትክክለኛው ቃል ፈልጎ ማግኘት ይከብዳል ብዙ አመት ከብዙ ትዝታዎች ጋር አሉኝ። ለትንሽ አመት ቢሆንም እዚ የመቆየት ሀሳብ ነበረኝ ግን እጣ ፈንታ የተለያየ መንገድ እንድንሄድ አቅጣጫችን የተለያየ እንዲሆን አድርጓል። ግን የሰጣችሁኝን ድጋፍ መቼም አልዘነጋውም እድገቴ እዚሁ ነው። ህልሜን እንደኖርኩት ነው የምቆጥረው 7 ምርጥ አመታትን በቱሪን አሳልፌያለሁ 12 ዋንጫዎችን እንዲሁም ማንም የኔ ነው የማይላቸው 115 ጎሎችን አስቆጥሬያለሁ።በከባድ ጊዜ ከጎኔ ለነበራችሁ ደጋፊዎች ፣ ተጫዋቾች ፣ አሰልጣኞች ፣ የህክምና ክፍል አባላት በጣም አመሰግናለሁ። ዛሬ በዚህ ማልያ የመጨረሻ ጨዋታዬን አደርጋለሁ ቀላል ባይሆንም ግን ጭንቅላቴን ቀና አድርጌ ፣ ፈገግ ብዬ ለመጫወት እሞክራለሁ። ሲል በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።
ሚካኤል ደጀኔ።