ቅ/ጊዮርጊስ መሪነቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።

የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 24ኛ ሳምንት ዛሬ በተካሄደ የእለቱ የመጨረሻ መርሀ-ግብር።

▪️   ጅማ አባ ጅፋር 0-1 ቅ/ጊዮርጊስ
                    57’⚽️ ጋቶች ፓኖም

▪️የደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ የሚገኝ እና ላለመውረድ ጥረት እያደረገ የሚገኝ ቡድንን ያገናኘው መርሀ-ግብር በቅ/ጊዮርጊስ አሸናፊነት ተጠናቋል። መሪነቱን ያጠናከረበት ውጤት አስመዝግቧል።

▪️በ56ኛው ደቂቃ ላይ የጅማ አባ ጅፋር ግብ ጠባቂ አላዛር ማርቆስ ከ16:50 ውጪ ኳስ በአሰጁ በመንካቱ ከሜዳ በቀይ ካርድ ተሰናብቷል።

▪️ከጨዋታው በኋላ የሁለቱ ቡድን አሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

▪️ቅ/ጊዮርጊስ ነጥቡን 54 በማድረስ መሪነቱን ያጠናከረበትን ውጤት ሲያስመዘግብ ጅማ አባ ጅፋር በበኩሉ በ19 ነጥብ ባለበት 15ኛ ደረጃ ለመቀመጥ ተገዷል።

▪️የቅ/ጊዮርጊስ ምክትል አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ 🗣 ከባድ ጨዋታ ነበር ፣ በፈለግንበት ሰአት ላይ ጎል አግብተናል። ነጥብ ጥለን ስለነበር የመጠሠነው የተጫዋቼ የማሸነፍ ጉጉት ነበራቸው በውጤቱም በጣም ደስተኛ ነኝ ብሏል። ለቀጣዩ የፋሲል ከተማ ጨዋታ ተዘጋጅተን የምንመጣ ይሆናል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

▪️የጅማ አባ ጅፋር አሰልጣኝ የሱፍ አሊ በበኩሉ  🗣 በራሳችን ስህተት ዋጋ ከፍለናል።የሚቀሩንን ጨዋታዎችን በማሸነፍ ላለመውረድ ጥረት እናደርጋለን ብለዋል።

▪️በቀጣይ ማለትም በ25ኛ ሳምንት ቅ/ጊዮርጊስ ከ ፋሲል ከተማ ጋር ሲገናኝ ጅማ አባ ጅፋር ከ አዲስአበባ ከተማ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

ሚካኤል ደጀኔ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.