ኤሲ ሚላን የራቀውን ስኩዴቶ ዋንጫ ሊያሳካ ተቃርቧል።

በጣልያን ሴሪያ በተካሄደ ተጠባቂ መርሀ-ግብር።

▪️ ኤሲ ሚላን 0-0 አታላንታ
57’⚽️ ሊያኦ
74’⚽️ ቲዮ ሄርናንዴዝ

▪️ ከ2010/11 የውድድር ዘመን ወይም ከ 11 አመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የስኩዴቱ ዋንጫ ለማንሳት ጥረት እያደረገ የሚገኘው ኤሲ ሚላን 1 እጁን ዋንጫው ላይ ያሳረፈበትን ውጤት አስመዝግቧል። የኤሲ ሚላን በተከታታይ ያልተሸነፈበትን 15 ጨዋታ መሆን ችሏል። የጃን ፒዬሮ ጋስፔሪኒው አታላንታ ጥሩ ፉክክር ቢያደርግም ከእረፍት መልስ በፖርቹጋላዊው ታዳጊ ተጫዋች ራፋኤል ሊያኦ እና በፈረንሳዊው ቲዮ ሄርናንዴዝ ግብ ታግዘው ወሳኝ 3 ነጥብ በሜዳቸው ሳንሲሮ ጁሴፔ ሜዛ አስተናግደዋል።

▪️ 5 ተከታታይ ጨዋታዎችን ያሸነፉት ኤሲ ሚላኖች በቀጣይ ሳምንት ወደ ስታዲዮ ማፔ አቅንተው ከሳሱሎ ጋር ነጥብ መጋራት ብቻ ለ19ኛ ጊዜ ስኩዴቶውን ከፍ አድርገው ማንሳታቸውን ያረጋግጣሉ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.