ሊቨርፑል የውድድር ዘመኑን 2ኛ ዋንጫ አሳክቷል።

እ.ኤ.አ በ1871 የውድድር ዘመን እንደተጀመረ የሚነገርለት አንጋፋው የእንግሊዝ ውድድር ዘንድሮም ለ150ኛ ጊዜ የተካሄደው የኤፍ ኤ ካፕ ጨዋታ በዌምብሌይ ስቴዲየም ተካሂዷል። የአምና እና የዘንድሮው የፍፃሜ ተፋላሚዎቹ የምዕራብ ለንደኑ ቼልሲዎች 9ኛ ጊዜ ዋንጫውን ለማንሳት የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል በበኩሉ ለ8ኛ ጊዜ ዋንጫውን ለማንሳት በማሰብ ወደ ሜዳ ገብተዋል።

▪️ሊቨርፑል ከ 3 ወር በፊት በየካቲት ወር በሊግ ካፕ (በካራባኦ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ) ከቼልሲ ጋር ተገናኝተው በመለያ ምት 11-10 የመርሲሳይዱ ክለብ ማሸነፉ ይታወሳል።

▪️የመጀመሪያ አጋማሽ ኢላማቸውን የጠበቁ ሙከራዎችን ቼልሲ የበላይነት ቢይዝም በጨዋታ እንቅስቃሴ ሊቨርፑሎች የተሻሉ ነበሩ። የጨዋታው አነጋጋሪ ጉዳይ ግብፃዊው ኮኮብ ሞሀመድ ሳላህ በጡንቻ መሳሳብ ጉዳት በ32ኛው ደቂቃ ከሜዳ መሰናበቱ ነው። ከ2 ሳምንት በኋላ በፓሪስ ለሚካሄደው ተጠባቂው የሻምፒዮንስ ሊግ የዋንጫ ጨዋታ ይህ ጉዳይ መፈጠሩ የሊቨርፑል ደጋፊዎች ላይ ትልቅ ስጋትን አጭሯል።

▪️በሁለተኛው አጋማሽ ሊቨርፑል በተደጋጋሚ ጎል ለማስቆጠር ጥረት አድርገዋል። በኮሎምቢያዊው ልዊስ ዲያዝ እንዲሁም በግራ መስመር ተመላላሹ ሮቤርትሰን አማካኝነት ቋሚ ብረቱ የመለሰባቸው አጋጣሚዎች ነበሩ። መደበኛ 90 ደቂቃውም ያለ ምንም ግብ 0-0 በሆነ አቻ ውጤት ለመጠናቀቅ ተገዷል።

▪️በተጨመሩት 30 ደቂቃዎች ሁለቱም ቡድኖች ተጭኖ ግብ ለማስቆጠር ጥረት ከማድረግ ይልቅ ጥንቃቄን መሰረት ያደረገ ጨዋታ ለመጫወት ጥረት ያደረጉት ሁለቱም ቡድኖች ግብ ማስቆጠር ሳይችሉ ቀጥታ ወደ መለያ-ምት አምርተዋል። በመለያ ምቱም ሊቨርፑል 6-5 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ለ8ኛ ጊዜ የኤፍ ኤ ካፕ አሸናፊ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

▪️በቼልሲ በኩል ሴዛር አዝፕሊኬታ እና ሜሰን ማውንት ሲያመክኑ በሊቨርፑል በኩል ሳድዮ ማኔ የመለያ ምቱን መጠቀም ያልቻለ ተጫዋች ነው። አሰልጣኝ የርገን ክሎፕም በ2015 ክለቡን ከተረከቡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ይህንን ዋንጫ ማሳካት ችለዋል። ቼልሲ ለተከታታይ ሶስተኛ ጊዜ ለዋንጫው ቢደርስም የዋንጫ ፆዋውን መቅመስ አልቻለም።

ሚካኤል ደጀኔ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.