ግብ ጠባቂ ጎል በማግባት የተሳተፈበት ጨዋታ ።

የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት በባህርዳር ስቴዲየም መካሄዳቸውን ቀጥለዋል።

በአራት ሰአቱ ጨዋታ (4:00)

▪️ሲዳማ ቡና 3-5 መከላከያ
18’⚽️ ዳዊት ተፈራ              2’⚽️ ቢኒያም በላይ
73’90+3’⚽️⚽️
ይገዙ ቦጋለ                    4’41’⚽️⚽️ ተሾመ በላቸው
                                        53’⚽️ አዲሱ አቱላ
                                        68’⚽️  ክሌመንት ቦዬ

5ኛውን ጎል ለመከላከያ ያስቆጠረው በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እንግዳ የሆነ እና ብዙ ጊዜ በማይስተዋል መልኩ ግብ ጠባቂው ክሌመንት ቦዬ ሲሆን የሲዳማው ግብ ጠባቂ ተ/ማርያም ሻንቆ በአእምሮ ዝግጁ እንዳልነበር ያሳየ ነው። በሊጉ ከ2009 በኋላ ግብ ጠባቂ ጎል ሲያስቆጥር ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

▪️መከላከያ 3ኛ ተከታታይ ድሉን ሲያስመዘግብ ነጥቡንም 30 በማድረስ 3 ደረጃዎችን በማሻሻል 7ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

▪️ሲዳማ ቡና በበኩሉ የመሀል ተከላካዮቹ ያኩቡ መሀመድ እና ጊት ጋት ጉት በጉዳት በጨዋታው አለመሰለፋቸው የጎል ናዳ እንዲያስተናግዱ ምክንያት ሆኗል። በ34 ነጥብ ባሉበት 5ኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ተገደዋል።

▪️ከጨዋታው በኋላ ሁለቱም አሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

▪️የመከላከያው ምክትል አሰልጣኝ ዮርዳኖስ አባይ 🗣 5 እናገባለን ብዬ ባልጠብቅም እንደምናሸንፍ ገምቼ ነበር። ግን ዋናው ነገር ተጫዋቾቼ ላይ የማየው ተነሳሽነት እና ጥረት ነው ትልቁ ነገር ይህ ክለብ ደረጃው እዚ ጋር አይደለም በሚል ተነሳሽነት ልምምድ ላይ የምንሰራቸውን ስራዎች ጨዋታ ላይ በሚገባ እየተገበሩ የደረጃ ሰንጠረዡ ላይም ቡድኑን ከፍ እያደረጉት ይገኛሉ። ስለዚህ እነሱ ሊመሰገኑ ይገባል ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።

▪️የሲዳማ ቡናው አሰልጣኝ ገ/መድህን ሀይሌ በበኩሉ 🗣 ለኛ ጥሩ ውጤት አይደለም ፣ ተከላካይ መስመራችን በጣም ክፍት ነበር ፣ እንደዚ አይነት ጎል አስተናግጄ ተሸንፌ አላውቅም። ሀላፊነቱን እኔ እወስዳለሁ ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።

▪️በ24ኛው ሳምንት መርሀ-ግብር መከላከያ ከ ፋሲል ከተማ እንዲሁም ሲዳማ ቡና ከ ወላይታ ዲቻ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

ሚካኤል ደጀኔ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.