አዳማ ከተማ መጥፎ ሪከርድ ተጋርቷል።
▪️23ኛው ሳምንት ላይ የሚገኘው የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በባህርዳር ስቴዲየም መካሄዱን እንደቀጠለ ነው።
በእለቱየተካሄደው ሶስተኛ (የ10 ሰአቱ) ጨዋታ።
▪️አዳማ ከተማ 0-0 አርባምንጭ ከተማ
▪️በጨዋታው 65ኛው ደቂቃ ላይ የአርባምንጭ ከተማ ተጫዋች ተካልኝ ደጀኔ እንዲሁም ከአዳማው የፊት መስመር ተጫዋች አቡበከር ወንድሙ ጋር በነበራቸው ግጭት ጨዋታው ለተወሰኑ ደቂቃዎች ጨዋታው ተቋርጦ ነበር።
▪️ ተካልኝ ደጀኔ የተሻለ ህክምና ለማግኘት በአምቡላንስ ከሜዳ ወጥቷል።
▪️አዳማ ከተማ የውድድር ዘመኑ 15ኛ አቻ ውጤት አስመዝግቧል። ከዚ በፊት በ1 የውድድር ዘመን ብዙ አቻ ውጤት ያስመዘገበ ሁለተኛው ክለብ ሆኗል። ከዚ በፊት በ2003/04 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀረር ከተማ በአንድ የውድድር ዘመን 15 አቻ መውጣቱ የሚታወስ ነው። ከዛም በኋላ በ2009 መብራት ሀይል በአንድ የውድድር ዘመን 15 ጨዋታዎችን በአቻ ውጤት ማጠናቀቁ ይታወሳል ይህንን መጥፎ ሪከርድ አዳማ ከተማ ዛሬ ባደረገው የ23ኛ ሳምንት መርሀ-ግብር መጋራት ችሏል።
▪️ አዳማ ከተማ በ27 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ አርባምንጭ ከተማ 11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
▪️ከጨዋታው በኋላ ሁለቱም አሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
▪️የአዳማ ከተማው ፋሲል ተካልኝ 🗣 የመጀመሪያው አጋማሽ ቡድኔ ጥሩ ነበር። ሁለተኛው አጋማሽ ግን ጥሩ አልነበርንም ፣ ቡድኔ ጥሩ ነው ምናገኛቸውን እድሎች የመጠቀም
▪️የአርባምንጩ መሳይ ተፈሪ 🗣 ውጤቱ መጥፎ አይደለም ካለንበት ደረጃ ለማሻሻል ጥረት አድርገናል። ሁለተኛው አጋማሽ ላይ ብልጫዎች ወስደን ነበር ቢሆንም ግን ጨዋታውን ማሸነፍ አልቻልንም ብለዋል።
▪️በቀጣይ አርባምንጭ ከተማ ከሀዋሳ ከተማ እንዲሁም አዳማ ከተማ ከ ባህርዳር ከተማ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።
ሚካኤል ደጀኔ።