ሲቲ አንድ እጁን ዋንጫው ላይ አሳርፏል።
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በተካሄዱ ቀሪ መርሀ-ግብሮች።
▪️ ሊድስ 0-3 ቼልሲ
4’⚽️ ማውንት
55’⚽️ ፑልሲች
83’⚽️ ሉካኩ
▪️ካለፉት 3 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች 2 ነጥቦች ብቻ ያሳካው የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ወደ ኤለን ሮድ አቅንቶ ሙሉ 3 ነጥብ አሳክቶ መምጣት ችሏል።
▪️ሊድስ ዩናይትድ ጨዋታው በተጀመረ ገና በ4ኛው ደቂቃ በሜሰን ማውንት አማካኝነት ግብ ማስተናገዳቸው እና በ24ኛው ደቂቃ የፊት መስመር ተጫዋቸው ዳንኤል ጄምስ ቀይ ካርድ መመልከቱ ጨዋታውን ተራራ የመውጣት ያክል ከባድ ዳገት እንዲሆንባቸው አድርጓል። ዳንኤል ጄምስ ቀሪዎቹን የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በተመለከተው ቀይ ካርድ ምክንያት የማይጫወት ይሆናል።
▪️1 ጨዋታ ቀደም ብለው የተጫወተው የዮርክሻየሩ ክለብ ሊድስ ዩናይትድ በ34 ነጥብ 18ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
▪️ሌስተር ሲቲ 3-0 ኖርዊች ሲቲ
54’62’⚽️⚽️ ቫርዲ
70’⚽️ ማዲሰን
▪️ዋትፈርድ 0-0 ኤቨርተን
▪️ዎልቭስ 1-5 ማንቸስተር ሲቲ
11’⚽️ ዴንዶንከር 7’16’24’59’⚽️⚽️⚽️⚽️ ዴብራይን
83’⚽️ ስተርሊንግ
▪️ ወደ ሞሊኒው ያቀናው ማንቸስተር ሲቲ በ24 ደቂቃዎች ውስጥ ቤልጂየማዊው ኮኮብ ኬቭን ዴብራይን ባስቆጠራቸው 3 ግቦች ከዛም 1 ግብ በማከል 4-1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።
▪️ይህ ቤልጂየማዊ ያስቆጠራቸው 4 ጎሎች በማንቸስተር ሲቲ ማልያ ካደረጋቸው 305 ጨዋታዎች 85ኛ ጎል ሆነው ሲመዘገቡ 116 ኳሶችንም አመቻችሎ አቀብሏል። በአጠቃላይ በ201 ኳሶች ላይ አሻራውን ማሳረፍ ችሏል። ቀሪውን 1 ግብ ራሂም ስተርሊንግ ማስቆጠር ችሏል።
▪️ከጎሎቹም በኋላ በቅርቡ ክለቡን ለተቀላቀለው ኤርሊንግ ብራውት ሀላንድ በደስታ አገላለፁ አቀባበል አድርጎለታል።
▪️ማንቸስተር ሲቲ በ89 ነጥብ መሪነቱን አጠናክሯል። ከ ሊቨርፑል ጋር ያለው የነጥብ ልዩነትም ወደ 3 ከፍ ብሏል። በቀጣይ ወደ ለንደን ኦሎምፒክ ስቴዲየም አቅንቶ ዌስትሀምን የሚያሸንፍ ከሆነ የ2022/23 የውድድር ዘመን ሻምፒዮን መሆናቸውን ያረጋግጣሉ።
ሚካኤል ደጀኔ።