ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በጀርመን ጎዳናዎች።

▪️አዲዳስ በሚል ስም የሚጠራው ግዙፉ የትጥቅ አምራች ተቋም አዲዜሮ የተሰኘ የሩጫ ውድድር በጀርመኗ ከተማ ሄርዞጌናውራች አካሂዷል። በወንዶች በተካሄደው የ5 ኪሎ ሜትር ውድድር የሁለት ጊዜ የአለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮናው ኢትዮጵያዊው ዮሚፍ ቀጀልጃ 12:53 በመግባት የውድድሩን ለመጀመሪያ ጊዜ ከሮጡ አትሌቶች ፈጣኑን ሰአት ጭምር በማስመዝገብ በቀዳሚነት ውድድሩን አጠናቋል። በቅርብ ርቀት ሲከተለው የነበረው ኬንያዊያኑ ኒኮላስ ኪሜሊ እንዲሁም ሌቪ ኪቤት 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

▪️በሴቶች በተካሄደው የ5 ኪሎ ሜትር ውድድር ሰንበሬ ተፈሪ 14:37 በመግባት በቀዳሚነት ውድድሯን ስታጠናቅ በዚሁ ርቀት 14:53 በመግባት ከ 20 አመት በታች እና ከ18 አመት በታች የአለምን ሪከርድ የተቆጣጠችው ሌላዋ ኢትዮጵያዊት  መዲና ኤልሳ ሰንበሬን በመከተል 2ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። ኬንያዊቷ ሜርሲ ቼሮኖ 14:56 በመግባት ሶስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። ሌሎቹ ኢትዮጵያውያን መልክነት ውዱ እና ንግስት ሀፍቱ 4ኛ እና 5ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

ሚካኤል ደጀኔ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.