በደቡብ አፍሪካው ቱው ኦሽንስ አልትራ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አሸነፉ

በደቡብ አፍሪካ የሚዘጋጀው የቱው ኦሽንስ አልትራ ማራቶን ቀደም ሲል የተካሄደ ሲሆን በወንዶች ኢትዮጵያዊው አትሌት እንዳለ በላቸው 3 ሰዓት ከ9 ደቂቃ በመግባት በአንደኛነት ሲያጠናቅቅ የደቡብ አፍሪካ አትሌቶች የሆኑት ኒኮሲሆና እና ስቦኒሶ 2ኛ እና 3ኛ በመሆን አጠናቀዋል ።

ውድድሩ በሴቶችም ሲቀጥል ደቡብ አፍሪካዊቷ ስቴይን 3 ሰዓት ከ 29 ደቂቃ በመግባት በአንደኝነት ስታጠናቅቅ በሁለተኝነት ደግሞ ሌላኛዋ ደቡብ አፍሪካዊት ቫን ዘይል አጠናቃለች በሶስተኝነት ውድድሩን የደመደመችው ደግሞ ኢትዮጵያዊቷ አለምወርቅ ፍቃዱ ቦሾ 3 ሰዓት ከ34 ደቂቃ በመግባት ነው ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.