የ25ኛው የፔፕሲ አዲስ አበባ የማራቶን ውድድር በደማቅ ሁኔታ ተጠናቀቀ

የአዲስ አበባ አስተዳደር አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከሞሀ ለስላሳ መጠጦች ጋር በጋራ የሚያዘጋጀው የ25ኛው የፔፕሲ አዲስ አበባ የማራቶን ውድድርን ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ ከመስቀል አደባባይ በመነሳት ፍፃሜውን ሰሚት በማድረግ ዛሬ እሁድ ሚያዚያ 2/2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተከናውኗል ።

በዚህ የማራቶን ውድድር ላይ ከክለቦች 52 ወንድ፤ 24 ሴት በድምር 76 አትሌት የተሳተፉ ሲሆን፤ ከግል 31 ወንድ 6 ሴት አትሌቶች በድምር 37 አትሌቶች ከቬተራን ደግሞ 40 ወንድ 6 ሴት በድምር 46 አትሌቶች በአጠቃላይ 159 አትሌቶች የተሳተፉበት ውድድር ተካሂዳል።

25ኛው የፔፕሲ አዲስ አበባ ማራቶን ውድድር አሸናፊ
በወንዶች
1,ሀብታሙ አሠፋ ከፌደራል
ማረሚያ,
2,ደረጄ መርሻ ከፌ/ፖሊስ
3,ሥንታየሁ ለገሠ ከፌፖሊስ
በሴቶች
1,አሥካለ ጠና ከፌ/ፖሊስ
2,ወርቄ ደጉ ከ ፌማረሚያ
3,መገርቱ በለጠ ከፌ/ማረሚያ
በቡድን ወንድ
1,ፌ/ፖሊስ
2,ፌ/ማረሚያ
3,መከላከያ
በሴት የቡድን
1,ፌ/ማረሚያ
2,ፌ/ፖሊስ

ቬትራን
ከ50 ዓመት በታች
1,አሠፋ ጥላሁን
2,ደሣለኝ ተገኝ
3,ገዛኸኝ ገብሬ
ከ50 አመት በላይ
1,አብደላ ሱሊማን
2,ንጋቱ አጋ
3,አያሌው እዳለ
ሴቶች ከ50 አመት በታች
1,ኩሬ መገርሣ
2,ሩት ተበጀ
3,ሀይማኖት በቀለ

የውድድሩ የሽልማት መጠን

✔️በዋና አትሌቶች
1ኛ ለወጣ 8000 ብር
2ኛ ለወጣ 5000 ብር
3ኛ ለወጣ 3000 ብር
4ኛ ለወጣ 2000 ብር
5ኛ ለወጣ 1000 ብር
6ኛ ለወጣ 750 ብር

✔️ለቬተራን
1ኛ ለወጣ 3000 ብር
2ኛ ለወጣ 2000 ብር
3ኛ ለወጣ 1000 ብር

✔️ለኮኮብ አሰልጣኝ
3000 ብር

Leave a Reply

Your email address will not be published.