በኔዘርላንድ ሮተርዳም የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አሸናፊ ሆኑ

👉እ.ኤ.አ 1980 ጀምሮ መካሄድ የጀመረውና ዘንድሮ ለ41ኛ ጊዜ የተካሄደው እንዲሁም አለማችን ላይ ካሉ ፈጣን ሰአት ከሚመዘገብባቸው የማራቶን ውድድሮች መካከል አንዱ የሆነው የኔዘርላንድ ሮተርዳም የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አሸናፊ ሆነዋል።

👉በወንዶች ብርቱ ፉክክር የታየበት ውድድር የተካሄደ ሲሆን

▪️ለኔዘርላንድ የሚሮጠው አብዲ ነጋዬ 2:04:54 በመግባት በቀዳሚነት ውድድሩን ሲያሸንፍ ኢትዮጵያዊው ልኡል ገ/ስላሴ 2:04:55 እስከመጨረሻው ከአብዲጋ የተናነቀ ቢሆንም ሁለተኛ በመሆን አሸንፏል
▪️ኬንያዊው ኪፕዮጎ 2:05:10 በመግባት 3ኛ ደረጃን በመያዝ አሸንፏል።

👉በሴቶች በተካሄደው ውድድር

▪️ኢትዮጵያዊቷ ሀቨን ሀይሉ  2:21:59 በመግባት 1ኛ በመሆን አሸንፋለች።

▪️ኔዘርላንዳዊቷ ኒዬንካ ብሪንክማን 2:22:49 ሁለተኛ እንዲሁም

▪️ዛና ቱሪ ማማዛኖቫ 2:26:49 በመግባት 3ኛ ደረጃን በመያዛ አሸንፈዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.