የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር የውድድር እና ሥነ-ስርዓት ኢትዮጵያ ቡናና ቅዱስ ጊዮርጊስን ቀጣ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር የውድድር እና ሥነ-ስርዓት ኢትዮጵያ ቡናና ቅዱስ ጊዮርጊስን ቀጣ

በ17ኛ ሳምንት በተከናወኑ ጨዋታዎችም ላይ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር የውድድር እና ሥነ-ስርዓት በዲሲፕሊን ጉድለቶችን በመመርመር አጥፊዎች ያላቸውን አካላት ቀጥቷል።

በዚህም መሠረት በኢትዮጵያ ቡናና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ ላይ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች የቅዱስ ጊዮርጊስን አመራሮች በመዝለፋቸው ወንበሮችን ወደሜዳ ስለወረወሪ እንዲሁም 42 ወንበሮች የቆረጡ ፣ የተሰነጠቁ ፣የተነቀሉ ሆነው ስለተገኙ ሪፖርት በክለቡ ላይ ስለቀረበበት የክለቡ ደጋፊዎች ላጠፉት ጥፋትና ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ሁኔታ ክለቡ መቀጣቱን ታሳቢ በማድረግ ደጋፊዎቹም ሊታረሙ ባመቻላቸው ክለቡ የሰባ አምስት ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍል ተወስኗበታል።

የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎችም የተሰባበሩ ወንበሮችን ወደ ሜዳ በመወርወራቸው እንዲሁም 34 ወንበሮች የቆረጡ፣ የሰነጠቁ እና የተነቀሉ መሆናቸውን ሪፖርት ስለቀረበባቸው ሃያ አምስት ሺህ ብር ክለቡ እንዲከፍል ተወስኗል።

አዳማ ከተማም ከጅማ አባ ጅፋር ጋር ባከናወነው ጨዋታ ደጋፊዎቹ የእለቱን ዳኛ እንዱሁም የተጋጣሚ ቡድን አሰልጣኝን በመሳደባቸው ሃምሳ ሺህ እንዲከፍል ተወስኗባቸዋል።

የወላይታ ድቻ ቡድን መሪ አቶ ወንድሙ ሳሙኤል ክለቡ ከሀዋሳ ከተማ ጋር ባከናወነው ጨዋታ የእለቱን ዋና ዳኛን በመሳደቡ አምስት ሺህ ብር እንዲከፍሉ እና በስድስት ጨዋታ አገልግሎት እንዳይሰጡ ታግደዋል፡፡

በተጨማሪ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር የውድድር እና ሥነ-ስርዓት ኮሚቴ
ከፋሲል ከነማ ወልቂጤ ከተማ ባከናወኑት ግጥሚያ ላይ ፋሲል ከነማ በወልቂጤ ከተማ ያልተገቡ ባላቸው ተጫዋቾች ላይ ባቀረበው ክስ ውጤቱ ለጊዜው እንዲታገድ እና ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ማብራሪያ እንዲጠየቅ እና ውሳኔ እንዲሰጥ መወሰኑን አሳውቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.