ኢትዮጵያን በኳታሩ የአለም ዋንጫ የሚያስጠራት ጀግና አገኘች
ኢትዮጵያዊው ምርጥ ዳኛ ባምላክ ተሰማ ለኳታሩ የአለም ዋንጫ መመረጣቸው ተረጋገጠ። ።
የኳታር የአለም ዋንጫ በቀጣይ አመት ከህዳር 12 እስከ ታህሳስ 9 ድረስ ሲካሄድ በዳኝነት በውድድሩ ላይ ከሚሳተፉ አርቢትሮች መካከል ስምንቱ አፍሪካውያንን መሆናቸውን ይፋ ሲደረግ ከነዚህ ውስጥ በአፍሪካው ዋንጫ አስገራሚ ውጤት ያስመዘገበው ኢትዮጵያዊው ባምላክ ተሰማ አንዱ መሆኑን ፊፋ አሳውቋል።
ከኢትዮጵያዊው አመለ ሸጋው ጀግና ዳኛ👉ባምላክ ተሰማ በተጨማሪም በአለም ዋንጫው ላይ እንዲዳኙ የተመረጡ አፍሪካውያን
2.ቪክተር ጎሜዝ 👉ከደቡብ አፍሪካ
3.ጃኒ ሲካዝዌ 👉ከዛምቢያ
4.ማጉኤቴ ንዲያዬ👉 ከሴኔጋል
5.ጃኩኤስ ንዳላ👉 ከኮንጎ
6.ሙስጠፋ ጎርባል 👉ከአልጄሪያ
7.ሬዱያኔ ጅያድ 👉 ከሞሮኮ
8.ፓፓ ባካሪ ጋሳማ👉 ከጋምቢያ
መሆናቸው ተረጋግጧል።
👉👉👉👉
በደማቅ ፈገግታቸው የሚታወቁትና በስራቸው ታታሪና ቆፍጣና የሆኑት በአምላክ ተሰማ ከተጫዋቾች ጋር ግርግር እና ጭቅጭቅ ውስጥ መግባት የሚፈልጉ ዳኛ አይደሉም።
የማስጠንቀቂያ ቢጫ ካርድ አንዳንዴም ቀይ ካርድ ሲሰጡ በፈገግታ ታጅበው ነው ይህም ድርጊታቸው ብዙውን ግዜ በስነልቦናው ረገድ ተጨዋቾችን ለማረጋጋት ጠቃሚ የሆነላቸው ይመስላል ። የወደቀ ተጫዋች በማንሳት እና ከተጨዋቾች ጋር የቅርብ ትስስር በመፍጠርም ስራቸውን ከማቅለሉ በተጨማሪ ከበሬታን እንዲያገኙ አድርጓቸዋል ።
በ2018 የሩስያ አለም ዋንጫ ላይ በአራተኛ ዳኝነት ሀገራቸውን ወክለው የተመለሱት ባምላክ ተሰማ ከቀናት በፊትም ለአለም ዋንጫ ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታ ባማኮ ላይ ማሊ ከቱኒዚያ ያደረጉትን ጨዋታ በመሀል ዳኝነት መርተዋል።
በአምላክ ተሰማ በዚህ አመት በተከናወነው የአፍሪካ ዋንጫ ሴኔጋል ከጊኒ እንዲሁም አዘጋጇ ካሜሩን ከኮሞሮስ ያደረጉትን ጨዋታ በመሃል ዳኝነት ግብፅ ከናይጄሪያና እንዲሁም ግብጽ ከሱዳን ያደረገችውን ጨዋታ ደግሞ በአጋዥ ተንቀሳቃሽ ምስል [ቪኤአር] ዳኝነት መርተዋል።
የሴኔጋልና የከቡርኪና ፋሶ ለዋንጫ ለማለፍ ያደረጉትን ወሳኝ ፍልሚያ የመሩት ‘ኢንተርናሽናል’ አልቢትር ባምላክ ተሰማ የመገናኛ ብዙኃንና በማኅበራዊ ሚዲያ ከፍተኛ አድናቆትን ያተረፋ ነበሩ። በአለም ዋንጫስ ምን ይገጥማቸው ይሆን? ሀገራቸው ኢትዮጵያን በአፍሪካ እና በአለም ዋንጫ በማስጠራት ተደራራቢ ውክልናን የወሰዱት እኚህ ጀግና ዳኛ
የአፍሪካ ዋንጫው ጀግንነት በአለም ዋንጫም እንደሚደግሙት ጥርጥር የለውም።