ቡና ገበያ ተጨማሪ የስፖንሰርሺፕ ስምምነቶችን ማድረጉን ቀጥሏል

ኢትዮጵያ ቡና ከ ‘ሀ እስከ ፐ’ ጋር የማልያ ሽያጭ ርክክብ አከናውኗል።

▪️ በ2014ቱ ቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዙር ጀምሮ የሚጠቀምባቸው መለያዎች ለዕይታ ቀርበዋል።

▪️በዋናው ቡድን ፣ የሴቶች ቡድን ፣ ከ20 አመት በታች እንዲሁም ከ17 አመት በታች የሚለብሷቸው 500 ማልያዎች ርክክብ ተፈፆሟል።ሙሉ ቡኒ ቱታ ወደ 100 የሚሆን እንዲሁም የአሰልጣኞች አባላት የሚጠቀሙት 50 ቲሸርቶች ኢትዮጵያ ቡና የተረከበ ሲሆን በአጠቃላይ ወደ ገንዘብ ሲለወጥ 3 ሚሊዮን 25 ሺ ብር የሚሆን ነው።ኢትዮጵያ ቡና ወደ ሜዳ ይዞት በሚገባው ማሊያው እጅጌ ላይ “ሀ እስከ ፐ”  አርማው የሚያርፍ ይሆናል።

 

ሁለቱ ወገኖች ከሚዲያ አካላት ለቀረበላቸው ጥያቄ ማብራሪያ እና ምላሽ ሰጥተዋል።

በኢትዮጵያ ቡና የማልያ ሽያጭ ማዕከል ውስጥ ማልያዎቹ ሲሸጡ ገቢው የኢትዮጵያ ቡና ወይ “ከሀ እስከ ፐ” ነው?
“ሀ እስከ ፐ” ከማልያ ላይ ማስታወቂያ በተጨማሪ ሌሎች የማስታወቂያ ስራዎች ላይ ይሰራል ወይ? ዋናውን ማልያ አስመስለው የሚሸጡ ነጋዴዎች ከመከላከል አኳያ “ከ ሀ እስከ ፐ” ምን አስቧል በማለት ከኢትዮጵያን ስፖርት አዘጋጅ ተጠይቋል?

🗣 የማስታወቂያ ስራዎች እንደሚሰራ እና አስመስሎ የሚሸጡ ነጋዴዎች መከላከል ዙሪያ አስቸጋሪ እንደሆነ በመግለፆ ጫን ብሎ እየሰራ እንደሆነ እና እንዲሁም ደጋፊዎቹም በመተባበር ይህንን ችግር ይፈታሉ ብለው እንደሚያስቡ አቶ ገዛኸኝ ገልፀዋል። ከሁሉም ሽያጭ 20 በመቶ “ሀ እስከ ፐ” የሚያገኝ ሲሆን ከማልያ ሽያጮች የትርፍ ክፍፍል ከኢትዮጵያ ቡና ጋር እንደሚኖራቸውም አብራርተዋል። አያይዘውም በአንድ ወር ውስጥ ብራንድ ሾፕ የሚክፈት አላማ ያነገቡ ሲሆን በውስጡ ማልያ እና ቁምጣ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ቡና አርማ ያለበት ሰአት ፣ ሱፍ ወ.ዘ.ተ የሚሸጥ ይሆናል።

▪️ከጎፈሬ ትጥቅ አምራች ጋር አይጋጭም ለተባለው ጥያቄ? ቤት ኪንግ በክለቦች ቀለም ማሊያ እንደሚያሰራ ገልፆ ሁሉም ቡድኖች ተስማምተው ነበር። ግን የራሱን የቤት ኪንግ አርማን ከኋላ ወይም ከፊት ደረት ላይ እንዲደረግ ሲጠየቅ ቅ/ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና አንቀበልም ብለዋል ሌሎቹ ቡድኖች እንቀበላለን ላሉት በራሳቸው ቀለም ተሰርቶ በዚ ሳምንት ርክክብ ያደርጋሉ። ከጎፈሬ ጋር የሚጋጭ አይደለም። ሲሉ የክለቡ ፕሬዚዳንት መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ ገልፀዋል።

 

▪️ኢትዮጵያ ቡና ከሁለተኛው ዙር ጀምሮ የሚጠቀምባቸውን መለያዎች ባስተዋወቀበት መርሐ ግብር ላይ ከራይድ ትራንስፖርት ጋር የስፖንሰርሺፕ ስምምንት መፈፀሙ ሲገለፅ ዝርዝር ጉዳዮቹ በሌላ ሥነስርዓት ይፋ እንደሚደረጉ ተጠቁሟል።

 

 

 

ፈለቀ ደምሴ

Leave a Reply

Your email address will not be published.