በሀዋሳ እየተካሄደ ባለው የአትሌቲክስ ሻምፒዮና የውድድሩ ሪከርድ የተሻሻለበት ውጤት ተመዘገበ።

👉 3ኛው ቀኑን በያዘው 51ኛዉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በዛሬው ውሎ በርካታ ውድድሮችን አካሂዷል።

👉በሴቶች ዘርፍ በተካሄደ የምርኩዝ ዝላይ የፍፃሜ ውድድር።

▪️ሲፈን ሰለሞን  ከ ጥሩነሽ ዲባባ  2.10 ከፍታ በመዝለል 1ኛ ስትሆን

▪️ሜቲ ቤኩማ  ከ ጥሩነሽ ዲባባ  2.00  ከፍታ በመዝለል ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

👉በወንዶች በተካሄደ የዲስከስ ውርወራ ፍፃሜ ውድድር።

▪️ ማሙሽ ታየ ከ ሲዳማ ቡና  45.09  ርቀት በመወርወር የውድድሩን ሪከርድ በማሻሻል ጭምር በአንደኝነት ሲያጠናቅ

▪️ገበየሁ በ/ኢየሱስ  ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  43.77 ሜትር በመወርወር  2ኛ እንዲሁም

▪️ ኢብሳ ገመቹ ከ አዳማ ከተማ   42.85  ሜትር በመወርወር  3ኛ ደረጃ ይዞ አጠናቋል።

👉 በሴቶች የርዝመት ዝላይ ውድድር
ኪሩ ኢማን ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 5.75 ርቀት በመዝለል አንደኛ

▪️ማሬዋፒዶ ከመከላከያ 5.68 ርቀት 2ኛ እንዲሁም

▪️አርያት ዴቪድ ከ ኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ 5.68 ርቀት በመዝለል 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

👉 በወንዶች በተካሄደ የ110 ሜትር መሰናክል ውድድር

▪️ማረሰ ተስፋዬ ከ ኢትዮጵያ ንግድባንክ 14.06 በመግባት ቀዳሚ

▪️ኬሪዮን ሞርቴ ከ ኦሮሚያ ክልል 14.43 ሁለተኛ እንዲሁም

▪️ሮድቾል ከ ጥሩነሽዲባባ ማሰልጠኛ 14.76 ሶስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

👉በሴቶች 100 ሜትር መሰናክል ውድድር
▪️ሂርጰ ድርባ ከኦሮሚያ ክልል 14.08 በመግባት ቀዳሚ
▪️አለሚቱ አሰፋ  ከኦሮሚያ ክልል 14.17 በመግባት 2ኛ እንዲሁም
▪️ምህረት አሻሞ ከ መከላከያ 14.28 ሶስተኛ ደረጃ ይዘው ማጠናቀቃቸውን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ሚካኤል ደጀኔ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.