ኢትየጵያውያን በሮም በድል ተንበሸበሹ
▪️የሮም ማራቶን።
▪️እኤአ በ1995 የጀመረው እና ዘንድሮ ለ27 ጊዜ የተካሄደው የማራቶን ውድድር በውብ መልከአ ምድር እንዲሁም በሰው ሰራሽ ቅርሶቿ የምትታወቀው የጣልያኗ ዋና ከተማ ሮም ተካሂዷል።
▪️በአለምአፉ የአትሌቲክስ አወዳዳሪ አካል የብር ደረጃ የተሰጠው ይህ ውድድር ዘንድሮም ከ10,000 በላይ ተሳታፊዎችን አካቷል።
▪️በሴቶች አትሌት ሴቻለ ደለሳ አዱኛ 2:26:08 በሆነ ጊዜ በቀዳሚነት ስትገባ ኬንያዊቷ አትሌት ግላዲስ ጄሩቶ በ2:28:46 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ እንዲሁም ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ታደለች ነዲ በ2:31:00 ሰዓት በመግባት ሶስተኛ ወጥታለች።
▪️በወንዶች ደግሞ አኢትጵያዊው አትሌት ፍቅሬ በቀለ ተፈራ የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል በ2:06:48 በሆነ ሰዓት በመግባት በቀዳሚነት ውድድሩን አጠናቋል። ታደሰ ማሞ 2:07:04 ሁለተኛ እንዲሁም ሌላው ኢትዮጵያዊ አትሌት አብርሀም ግርማ በቀለ 2:08:31 በመግባት 3ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።