ሙክታር እድሪስ በስፔን ሪከርድ በማሻሻል አሸነፈ
የስፔን የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሂዷል።
▪️በየአመቱ የሚካሄደው ይህ ውድድር ዘንድሮም ለ 39 ጊዜ በስፔን ተካሂዷል። ጥር 9 ሊካሄድ ቀነ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረ ቢሆንም ከኮቪድ ወረርሺኝ ጋር ተያይዞ ውድድሩ ለ2 ወር ለመራዘም ተገዷል።
▪️ዘንድሮም ከ 14,000 በላይ የሚሆኑ አትሌቶች የተሳተፉበት ሲሆን የ2017 እና 2019 የአለም የ 5,000 ሜትር ሻምፒዮኑ ሙክታር እድሪስ የቦታውን ሪከርድ ጭምር በማሻሻል 28:31 በመግባት በአንደኝነት ውድድሩን አጠናቋል።