ጀግኖቹ ወደሀገራቸው ገቡ
በ18ኛው የአለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ውድድር ሃገራችን ኢትዮጵያ ለ17ኛ ጊዜ የተሳተፈች ሲሆን በአለም የቤት ውስጥ ውድድር ሃገራችን እ.ኤ.አ በ2008 ስፔን – ቫሌንሽያበተካሄደው ውድድር በ4 ወርቅ፣ 1 ብርና 1 ነሃስ በድምሩ 6 ሜዳልያ፣ እንዲሁም በ2018 እንግሊዝ – በርሚንግሃም በ4 ወርቅና 1 ነሃስ በድምሩ 5 ሜዳልያዎች የተገኙባቸው ጊዜያት ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገብንባቸው ወቅቶች ነበሩ፡፡
በዘንድሮው 18ኛው የቤልግደሬድ የአለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ሃገራችን 14 አትሌቶችን በማሰለፍ በ9 አትሌቶች 9 ሜዳልያዎች ከማግኘቷም በላይ በ4 ወርቅ፣ 3 ብርና 2 ነሃስ እንዲሁም በ2 ዲፕሎማ ከአለምም ከአፍሪካም ሻምፒዮናውን በአስደናቂ ሁኔታ በአንደኝነት ውድድሯን አጠናቅቃለች፡፡
በዛሬው እለት ረቡዕ መጋቢት 14/2014 ዓ.ም ከማለዳው 1፡20 ጀምሮ የቤልግሬዱን የአለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ልኡካን ቡድን በቦሌ አየር መንገድ፣ በአዲስ አበባ ልዩ ልዩ ጎዳናዎች እና በሸራተን አዲስ ሆቴል ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎችና አመራሮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች፣ እንዲሁም መላው የአትሌቲክስ ቤተሰብ በስፍራው በመገኘት እጅግ ደማቅ አቀባበል አድርገዋል፡፡
አትሌቶቹ ከቦሌ አየር መንገድ ውጥተው በአዲስ አበባ ጎዳናዎች በተዘዋወሩበት ጊዜም አትሌቲክስ ወዳዱ ህዝባችን አደባባይ ወጥቶ ደመቅ ያለ ሞራል እና ድጋፍ አሳይቷል።
▪️የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ጥሪ ለተደረገላቸው እንግዶች እዚ በመገኘታቸው በማመስገን ለተጎናፀፍነው ድል እንዲሁም ኢትዮጵያ አንገቷን ቀና ያደረጉትን ወርቅዬ አትሌቶቻች ባስመዘገቡት ድል ክብር እንደሚገባቸው እና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ መደሰቱንም በመግለፆ የውጭ ጣልቃ-ገብነትን በመቃወም ሀገራችን ወደ ቀድሞ ሰላሟ እንድትመለስ ጥሪ አስተላልፈዋል። ለዚህም የሁላችንም ሀላፊነት እንደሚሻ እና ስፖርቱ ዘር ፣ ሀይማኖት ፣ ቀለም ፣ ብሄር የማይለይ የሰላም መድረክ መሆኑንም አስገንዝበዋል።
▪️በ3000 ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ለሀገሯ ያበረከተችው እና በአለም መድረክ ሰንደቅ አላማዋ ከፍ እንዲል ካደረጉ አትሌቶች መካከል አንዷ የሆነችው አትሌት ለምለም ሀይሉ አሰልጣኟ ህሉፍ ይህደጎ ያላትን መመሪያዎች በመቀበል እና በመተግበር ይህን ድል መጎናጸፍ መቻሏን አስታውቃለች።
▪️በ1,500 ሜትር ሌላ ወርቅ ለሀገሯ ያበረከተችው እና 3:57:19 በመግባት የቦታውን የውድድር ሪከርድ ማሻሻል የቻለችው ጉዳፍ ፀጋዬ በበኩሏ ከጓደኞቿ ጋር በህብረት መስራቷ ውጤቱ እንዲሳካ ምክንያት መሆኑን ገልፃ ከጎኗ ለነበሩት ለአሰልጣኟ ህሉፍ ይህደጎ እንዲሁም ለሀኪሞች ምስጋና አቅርባለች።▪️ለውድድሩ ካስመረጣቸው 5 አትሌቶች 2 ወርቅ ፣ 1 ብር እና 1 ነሀስ ማስመዝገብ የቻለው አሰልጣኝ ህሉፍ ይህደጎ በበኩላቸው ለተደረገላቸው አቀባበል አመስግነው አትሌቶቹ ብዙ አስቸጋሪ ነገሮችን ተቋቁመው እዚ በመድረሳቸው ክብር እንደሚገባቸው ገልጿል።ለ18 ወራት ቤተሰቦቻቸውን ማየት እንዳልቻሉ እና በብዙ ጫና ውስጥ ሆነው ውድድሩን ማካሄዳቸውን ገልፆ ለሀገር ሰላም ጥሪውን አስተላልፏል።▪️በ3000 ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ለሀገሩ ያበረከተው ሰለሞን ባረጋ በበኩሉ ሀገርን ወክሎ የህዝብ አደራን ተሸክሞ ውድድሮችን ማካሄድ ከባድ መሆኑን ገልፆ ክለቡ ደቡብ ፖሊስ እንዲሁም አሰልጣኞቹን የሀገር ውድድሮች ላይ እንዲያተኩር እና መርሀ-ግብሮች እንዳይደራረቡበት ስላደረጉ በማመስገን ማንም ሰው በተሰማራበት ስራ ላይ ካተኮረ ማይሳካ ምንም ነገር እንደሌለ አስታውሷል። እንዲሁም በቦታው ለተገኙት ለኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን መልካም እድል ምኞቱን ገልፆል።
ወርቅ ሚዳሊያ ያስገኙ
1.ሳሙኤል ተፈራ በ1,500ሜትር 3.32.77 በመግባት ሪከርድ አሻሽሏል 👉በ
አሰልጣኝ ብርሀኑ መኮንን
2.ሰለሞን ባረጋ በ3,000ሜትር 👉አሰልጣኝ ኮማንደር ሁሴን ሼቦ
3.ጉዳፍ ፀጋዬ ቀ1,500ሜትር 3.57.19 ሪከርድ አሻሽላለች👉 አሰልጣኝ ህሉፍ_ይደጎ
4.ለምለም ሀይሉ 3,000👉አሰልጣኝ ህሉፍ_ይደጎ
ብር ሜዳሊያ
1.አክሱማዊት እምባዬ በ1,500ሜትር👉አሰልጣኝ ኢንስፔክተር ወንድዬ
2.ለሜቻ ግርማ በ3,000ሜትር👉አሰልጣኝ ተሾመ
3.ፍረወይን ሀይሉ በ 800ሜትር👉በአሰልጣኝ ህሉፍ_ይደጎ
ነሀስ ሜዳሊያ
1.ሂሩት መሸሻ በ1,500ሜትር👉አሰልጣኝ ህሉፍ_ይደጎ
2.እጅግ አየሁ ታዬ በ3,000ሜትር👉አሰልጣኝ ሀብታሙ
ዲፐሎማ ያገኙ
ታደሰ ለሚ በ1,500ሜትር 4ኛ
ዳዊት ስዩም በ3000 ሜትር 5ኛ
ሀብታም አለሙ በ800ሜትር 7ኛ