የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣርያ የኡጋንዳ አቻውን አሸንፎ አለፈ
▪️የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣርያ አንደኛ ዙር የመልስ ጨዋታ ዩጋንዳን ዛሬ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም 10፡00 ።
በመጀመርያው ጨዋታ ዩጋንዳ ላይ ሁለቱ ቡድኖች 2-2 መለያየታቸው አይዘነጋም።
ድል ለ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድናችን 🇪🇹
የኡጋንዳ 🇺🇬 ብሄራዊ ቡድን መዝሙር እየተዘመረ ይገኛል።
የኢትዮጵያ 🇪🇹 ብሄራዊ ቡድን መዝሙር እየተዘመረ ይገኛል።
1′ ጨዋታው ተጀመሯል።
5’ጨዋታው አንፃራዊ በሆነ መልኩ የዩጋንዳ ብሄራዊ ቡድን ኳስን በመቆጣጠር ብልጫ ወስደው እየተጫወቱ ይገኛሉ።
10′ ኢትዮጵያ 0-0 ኡጋንዳ
15′ ሁለቱም ቡድኖች በሙከራ ረገድ ቀዝቀዛ የሆነ እንቅስቃሴ እያሳዩ ይገኛሉ።
17′ ጨዋታው በአቻ ውጤት እንደቀጠለ ይገኛል።
20’ኢትዮጵያ 0-0 ኡጋንዳ
▪️ጨዋታው በዚ ውጤት የሚጠናቀቅ ከሆነ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንጨወደ ቀጣይ ዙር ማለፉን ያረጋግጣል።
25′ ኢትዮጵያ 0-0 ኡጋንዳ
▪️ጥንቃቄ ላይ መሰረት እና ትኩረት ያደረገ ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች እየተጫወቱ ይገኛሉ።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የተከላካይ መስመር ተጫዋቿ አንበሏ መሰረት ማሞ የመጀመሪያውን ቢጫ ካርድ ተመልክታለች።
ኡጋንዳ ብሄራዊ ቡድን ግብ አስቆጥሯል ⚽️
8 ቁጥሯ ሻኪራ የጎሉ ባለቤት ናት !!
35′ ኢትዮጵያ 0-1 ኡጋንዳ
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አቻነቷን ግብ ለማግኘት ያን ያህል ጥረት እያደረገ ነው ለማለት ይከብዳል። ኳስ መስርተው ለመጫወት እየተቸገሩ ኘው የሚገኙት።
በድምር ውጤት 3-2 እየተመራም ይገኛል።
40’ኢትዮጵያ 0-1 ኡጋንዳ
የመጀመሪያውን ቅያሪ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እያደረገ ይገኛል።
👇ፀሀይነሽ ጁላ ወጥታ
👆ደመቀች ዳልጋ ተክታት ገብታለች።
የመጀመሪያው 45 ደቂቃ ተጠናቆ የባከነ 1 ደቂቃ በ4ኛዋ ዳኛ ተጨምሯል።
የመጀመሪያው 45 ደቂቃ ተጠናቋል።
ኢትዮጵያ 0-1 ኡጋንዳ
▪️2ኛው አጋማሽ ተጀምሯል።
50′ ኢትዮጵያ 0-1 ኡጋንዳ
55’የኡጋንዳ ብሄራዊ ቡድን የመጀመሪያ ቅያሪውን እያደረገ ይገኛል።
56′ ከእረፍት መልስ በአንፃራዊነት ጥሩ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የዩጋንዳ ብሄራዊ ቡድን የተከላካይ መስመርን በማስከፈት አደገኛ ሙከራዎችን ማድረግ አልቻለም።
56′ ኢትዮጵያ ዐ-1 ኡጋንዳ
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ሁለተኛ ቅያሪውን አድርጓል።
👇መስከረም ወጥታ
👆ሰሚራ ከማል ተክታት ገብታለች።
60’ኢትዮጵያ 0-1 ኡጋንዳ
▪️የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በባለፈው ጨዋታ አንድ ግብ ያስቆጠረችውን ሰሚራ ከማልን ቀይረው ቢያስገቡም ያን ያህል የዩጋንዳዋን ግብ ጠባቂ ዳፊን ኒያዬንጋን የፈተና ሙከራ ማድረግ አልቻሉም።
▪️ጨዋታው በዚ ውጤት የሚጠናቀቅ ከሆነ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ቀጣዩን ዙር መቀላቀል አይችልም።
70’ኢትዮጵያ 0-1 ኡጋንዳ
3ኛውን ቅያሪ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እያደረገ ይገኛል።
👇እምወድሽ ወጥታ
👆 ሰብለወንጌል ወዳጆ ተክታት ገብታለች
75′ ኢትዮጵያ ዐ-1 ኡጋንዳ
👉የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ወርቃማ እድል አመከነ።
የኡጋንዳ ግብ ጠባቂ ዳፊን ኒያዬንጋ የተፋችውን ኳስ ተቀይራ የገባችው ሰብለወንጌል ወዳጆ ወደ ግብ መቀየር አልቻለችም።
83’ኢትዮጵያ ግብ አስቆጠረች ⚽️ 👏👏
ከተከላካይ ጀርባ የተጣለን ኳስ እየሩሳሌም ወንድሙ በአግባቡ በመጠቀም ብሄራዊ ቡድናችንን አቻ አድርጋለች።
87′ ኢትዮጵያ 1-1 ዩጋንዳ
ኢትዮጵያ በድምር ውጤት 3-3 መሆን ችላለች። ይህ ውጤት ወደ ቀጣይ ዙር የሚያሳልፋት ይሆናል።
90’ኢትዮጵያ 1-1 ኡጋንዳ
መደበኛው 90 ደቂቃ ተጠናቆ 4 የባከነ ደቂቃ ተጨምሯል።
👉ግብ ጠባቂያችን አበባ አጄቦ ቢጫ ካርድ ተመልክታለች።
👉 ጨዋታው ተጠናቋል።
👉 ኢትዮጵያ በድምር ውጤት 3-3 በመውጣት እና ከሜዳ ውጪ ብዙ ግብ በማስቆጠር ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉን አረጋግጧል።
👉 በቀጣይ የደቡብ አፍሪካ አቻውን የሚገጥም ይሆናል።