ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተአምራታቸው እንደቀጠለ ነው ሳሙኤል ተፈራ የሀይሌን ሪከርድ ሰበረ።

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በቤልግሬድ ተአምራታቸው እንደቀጠለ ነው።

👉በሰርቢያ – ቤልግሬድ በሚካሄደው 18ኛው የአለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ1,500 ሜትር ወንዶች ፍፃሜ ውድድር ሳሙኤል ተፈራና ታደሰ ለሚ ኢትዮጵያን ወክለው ከተፎካካሪዎቻቸው ጋር ተፋልመዋል፡፡

ሳሙኤል ተፈራ 3:32:77 በመግባት የሻፒዮንስ ሺፑን ሪከርድ ጭምር በማሻሻል ለሀገሩ ወርቅ ሜዳሊያ አበርክቷል። ሀይሌ ገብረስላሴ 3.33.77 ይዞት የቆየውን ሪከርድ ሰብሮታል።

ውድድሩ የማሸነፍ ግምት የተሰጠው የኦሎምፒክ ሻምፒዮኑ ኖርዌያዊው ጄኮፕ ኢንግብሪጊስተን 3:33;02 በመግባት 2ኛ ሆኗል ኖርዊያዊው ጃኮፒ እንደሚያሸንፍ በሰፊው የተጠበቀ ቢሆንም ጀግናው ሳሙኤል ተፈራ በአስደናቂ አጨራረስ አሸንፎታል።

ሌላው ኢትዮጵያዊ ታደሰ ለሚ 3:33:59 በመግባት 4ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

ኢትዮጵያ 4ኛ ወርቅ 3ብር 2 ነሀስ በማግኘት በውድድሩ ያገኘችውን ሜዳሊያ 9 አድርሳለች።

#ፈለቀ_ደምሴ

Leave a Reply

Your email address will not be published.