ኢትዮጵያዊቷ ፍሬወይኒ በአስደናቂ አጨራረስ አሸነፈች
ኢትዮጵያውያን በቤልግሬድ አልተቻሉም
በሰርቢያ – ቤልግሬድ በሚካሄደው 18ኛው የአለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ፍሬወይኒ ሀይሉ በአስደናቂ አጨራረስ በ800 ሜትር 2:00:52 በመግባት ሁለተኛ በመውጣት ለሀገሯ ያልተጠበቀ ውጤት በማስመዝገብ አሸንፋለች።
በዚህ ውድድር አሜሪካዊቷ ሜሪካዊቷን ኤጄ ዊልሰን 1:59.09 በመግባት
አንደኛ በመሆን ያሸነፈች ሲሆን ፍሬወይኒ ሀይሉ ከመጨረሻው ረድፍ አጨራረሷን በማሳመር ከፊቷ ሲመሩ የነበሩትን በርካታ አትሌቶች እያለፈች በመጨረሻም ሁለተኛ መሆኗን አረጋግጣ የነበረችውን ኡጋዳዊቷን ጭምር በመቅደም ያሸነፈች ሲሆን ምናልባት ትንሽ ቀድማ ብትወጣ ኖሮ አሜሪካዊቷን ኤጄ ዊልሰን በመቅደም የምትችልበት ተስፋ ነበር ኢትዮጵያዊቷ ሀብታም አለሙ 2:03:37 በመሆን ውድድሩን አጠናቃለች።
ኢትዮጵያ በውድድሩ ያገኘችው አጠቃላይ ሜዳሊያ ወደ 8 ከፍ ብሏል።
🥇 🇺🇲 Ajee Wilson 1:59.09 SB
🥈 🇪🇹 Freweyni Hailu 2:00.54 SB
🥉 🇺🇬 Halimah Nakaayi 2:00.66