ኢትዮጵያውያኑ ጀግኖች ሰርቪያ ላይ ከትመዋል

የኢትያጽያ አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድን ለ 18ኛው የአለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ውድድሩን ወደ ምታዘጋጀው ሰርቢያ በሰላም ደረሰ።

ብሔራዊ ቡድኑ በአሀን ስዓት ከዋናው ከተማው በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው (Mona Plaza Guest) ላይ ከትሟል።

መጋቢት 6/ 2014 ዓም ምሽት 12:00 ላይ በቤሊቪው ሆቴል ክቡር አምባሰደር መስፍን ቸርነት የኢፌድሪ የባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስቴር፣ የ ኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ የፌደሬሽኑ የስራ አስፈፃሚና የአመራር ኮሚቴ አባላት እንዲሁም ጥሪ በተደረገላቸዉ አካላት ሽኝት የተደረገለት ኢትዮጵያን ወክለው ባለም የቤት ውስጥ እትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፉት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድን አባላት አስራ ስምንተኛውን የአለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮናን በምታስተናግደው ሰርቢይ ቤልግሬድ  በሀገሩ ስዐት 6:30 ላይ በሰላም ደርሷል። ማረፊያውን ከዋናው ከተማው የአንድ ስሜት እርቀት ላይ በሚገኘው (Mona Plaza Guest) አድርጓል።

መረጃው የኢአፌ ነው

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.