ከቻይናዋ የተነጠቀው የአለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሰርቢያ ሊደረግ ነው።

እ.ኤ.አ በ1987 በአለምአቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀባይነት በማግኘት በፈረንሳይ ከተማ ፓሪስ መካሄድ የጀመረው ይህ የአለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በየሁለት አመቱ ይከናወናል ።

ዘንድሮም ለቻይናዋ ከተማ ናንጂንግ የማዘጋጀት እድሉ ቢሰጣትም በአዲሱ ኖቬል ኮሮና ቫይረስ ስጋት ምክንያት አለማቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለአትሌቶች እንዲሁም አሰልጣኞች ፣ የሚዲያ አካላት በአጠቃላይ ስፖርቱ አደጋ ውስጥ እንዳይገባ ቀድሞ ከመጠንቀቅ ጋር ተያይዞ አዘጋጅነቱን ለሰርቢያ መስጠቱ ይታወሳልል። ሰርቢያም በዋና ከተማዋ ቤልግሬድ በሚገኘው ስታርክ አሪና ውድድሮቹን ለማስተናገድ ዝግጅቷን ጨርሳ እንግዶቿን እየተጠባበቀች ትገኛለች።

▪️ከመጋቢት 9-11 ለሚካሄደው ውድድር ከ150 ሀገራት የተወጣጡ ከ1000 በላይ አትሌቶች ውድድሩን እንደሚካፈሉ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ልዑካን ቡድንም ባሳለፍነው ወር በፈረንሳይ ከተማ ሊዬቪን የአለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድር ክብረ-ወሰንን በማሻሻል የግሏ ያደረገችው ጉዳፍ ፀጋዬን ጨምሮ በርካታ አትሌቶች ይካፈላሉ። የልዑካን ቡድኑ ዛሬ ከሌሊቱ 10:30 ጀምሮ ወደ ስፍራው እንደሚያቀና ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.