በአውሮፓ መድረክ ሀያሉ ክለብ የፈረንሳይ ከተማውን ክለብ ትንሽነቱን ያሳየበት ምሽት።

የሁለቱ ቡድኖች ታሪክ ወደ 1956 ይመልሰናል። የ13ጊዜ የሻምፒዮንስ ሊግ ክብርን ተጎናፆፈው የአውሮፓ ንጉሶች የተባሉት ሎስ ብላንኮዎቹ በ1956 በአሁኑ የፓሪስ ሴንት ጄርሜ ሜዳ ፓርክ ዴ ፕሪንስ ላይ ነበር የመጀመሪያ ዋንጫቸውን ማንሳት የቻሉት።

ከዛን ጊዜ ወዲህ በተደጋጋሚ በሻምፒዮንስ ሊጉ ልክ እንደ ሪያል ማድሪድ ሀያል ለመሆን እንዲሁም ዋንጫዎችን ለማንሳት ቢሞክሩም በአውሮፓ መድረክ የፈረንሳይ ከተማ ክለብ እንጂ ሀያል የሚለውን ክብር ማግኘት አልቻሉም።

የሪያል ማድሪዱ አሰልጣኝ ካርሎ አንቼሎቲ የመሀል ሜዳውን ደጀን ካሴሚሮን እንዲሁም የግራ መስመር ተከላካዩን ፈርላንድ ሜንዲን በቅጣት የሚያጡ ሲሆን በወጣቱ ኡራጋዊ ፌዴ ቫልቬርዴ እንዲሁም ሜንዲን ብዙ የመጫወት እድልን በማያገኘው ናቾ ፈርናንዴዝ ተክተው ወደሜዳ ገብተዋል። አሳሳቢ የነበረው የመሀል ሜዳው የቶኒ ክሮስ ጉዳይም በመጨረሻ ደቂቃዎች በሀኪሞች አዎንታዊ ምላሽ ታግዞ ቋሚ 11ዱን ተቀላቅሏል።

የፒ ኤስ ጂ አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ በበኩላቸው ዋመኛው ጥያቄ የነበረው የኪሊያን ምባፔ ጉዳይ እልባት አግኝቶላቸው በቋሚነት አሰልፈውት እንደተለመደው የፊት መስመሩን አደራ ሰጥተውታል።

▪️የመጀመሪያዎቹ 10 ደቂቃዎች በፍጥነት የታጀበ ፈጣን እንቅስቃሴ በሁለቱም ቡድኖች የተንፀባረቀበት ነበር። ኪልያን ምባፔ ላይ የተንጠለጠለ የሚመስለው የፒ ኤስ ጂ አጨዋወት አሁንም ኮርቱዋን ሲፈትን ተስተውሏል። ይህም አጨዋወት ቀጥሎ በዚህ አስደናቂ ፈረንሳዊ 38ኛው ደቂቃ ላይ ቀዳሚ መሆን ችለዋል።ኳሷን አመቻችቶ ያቀበለው ኔይማር ጁኒየር በሻምፒዮንስ ሊጉ ለምባፔ አመቻችቶ ያቀበላቸውን ኳሶች ወደ 7 አድርሷል።የመጀመሪያው 45 ደቂቃም በፒኤስ ጂ 1-0 መሪነት ተጠናቋል።

▪️ከእረፍት መልስ ብዙም የእንቅስቃሴ ለውጠሰ ያላሳዩት ሎስ ብላንኮዎቹ አሴንሲዮን በካማቪንጋ እንዲሁም ቶኒ ክሮስን በ ሮድሪጎ ተክተዋል።በ60ኛው ደቂቃ ላይ ግብጠባቂው ዶናሩማ የፈፀመውን ስህተት በሚገባ ካሪም ቤንዜማ በመጠቀም ሎስብላንኮዎቹን አቻ ማድረግ ችሏል።

▪️ከዚህ ግብ ከመቆጠር በኋላ ሪያል ማድሪድ በመነቃቃት እና ኳስ በመቆጣጠር በተደጋጋሚ መሪ የሚሆኑበትን እድል ለመፍጠር ሞክረዋል። ዳኒ ካርቫሀልንም በሉካስ ቫስኬዝ ተክተው አስገብተዋል። 76ኛው ደቂቃ ላይ የኔይማርን ኳስ በመንጠቅ መልሶ ማጥቃቱን ያስጀመረው ሉካ ሞድሪች አመቻችቶ ያቀበለውን ኳስ ካሪም ቤንዜማ አስቆጥሮ ቡድኑን በድምር ውጤት አቻ እንዲሆን አደረገ 2 ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እንደገና ካሪም ቤንዜማ ኳስን ከመረብ በማዋሀድ የማይታመን ገድል ፈፀመ። 500ኛ ጨዋታውን ለሪያል ማድሪድ ባደረገበት ምሽት ለራሱ በምሽቱ 3ኛውን ለቡድኑ ደግሞ ሩብ ፍፃሜውን እንዲቀላቀል ያስቻለች ግብ አስቆጠረ። የማይታመን የውጤት ቅልበሳ በሳንቲያጎ ቤርናቦ።

ሪያል ማድሪድ በድምር ውጤት 3-2 በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል።

ሚካኤል ደጀኔ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.