የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች እንዲሁም ከ18 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና።

▪️ዘንድሮ ለ10ኛ ጊዜ የሚካሄደው ከ20 አመት በታች እንዲሁም ዘንድሮ ለ3ኛ ጊዜ የሚካሄደው ከ18 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከሚያዝያ 28 እስከ መጋቢት 4 ድረስ በአሰላ ከተማ ይካሄዳል። እዚህ ውድድር ላይ የሚሳተፉ አካላት በአለም አትሌቲክስ አሰንዲሁም በፌዴሬሽኑ ህግና ደንብ መሰረትየኮቪድ ክትባት እንዲሁም የምርመራ ውጤት ማሳየት እንደሚጠበቅባቸው አስታውቋል። የቅድመ ውድድር ቴክኒካዊ ስብሰባውንም በዛሬው እለት በአሰላ ከተማ አካሂዷል።

▪️የውድድሩ ዋና አላማ በሀገራችን የሚገኙ አቅሙና ችሎታው ያላቸው የነገ ተተኪ አትሌቶችን በብቃት እና በጥራት በማፍራት ኢትዮጵያን በአለም አትሌቲክስ አደባባይ ሰንደቋን ከፍ የሚያደርጉና ብሄራዊ መዝሙሯን የሚያዘምሩ ውጤታማ አትሌቶችን ማፍራት እንደሆነ ያስታወቀው ፌዴሬሽኑ ሁሉም ተሳታፊ ክልሎች ፣ ከተማ አስተዳደሮች ፣ አትሌቲክስ ክለቦች እና ቡድኖች በትክክለኛ እድሜያቸው ብቻና ብቻ እንዲወዳደሩ በማድረግ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ በማሳሰብ ለውድድሩ የሚያልፊ አትሌቶች የእድሜ ተገቢነት ችግር ውስጥ ቢገቡ ፌዴሬሽኑ ሀላፊነት እንደማይወስድ ግን አስተማሪ የሆነና የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል። የውድድሩ መርሀ-ግብር ከታች በምስሉ ተያይዟል።

ፈለቀ ደምሴ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.