ኬንያውያን አትሌቶች የቶኪዮ ማራቶን ድል ቀንቷቸዋል።

▪️ከ7 ወር በፊት በዚሁ መድረክ የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ማሸነፍ የቻለው ኤሊውድ ኪፕቾጌ ዛሬ በቶኪዮ የተካሄደውን የማራቶን ውድድር 2:02:40 በመግባት ቀዳሚ ሆኖ አጠናቋል። ይህ የ 37 አመት ኬንያዊ 4ኛ ምርጡ ሰአቱን ማስመዝገብ ችሏል። እስከ 36ኪሎ ሜትር ድረስ  ሌላው ኬንያዊ አሞስ ኪፕሩቶ ኪፕቾጌን ሲከተል የቆየ ቢሆንም ኪፕቾጌ ልምዱን ተጠቅሞ ማሸነፍ ችሏል። ኢትዮጵያዊው ታምራት ቶላ 2:04:14 በመግባት 3ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቅ ችሏል።

▪️በሴቶች ዘርፍ ኬንያዊቷ ብሪጅድ ኮሴጊ 2:16:02 በመግባት ቀዳሚ ስትሆን የ2019 በርሊን ማራቶን አሸናፊዋ ኢትዮጵያዊቷ አሸተ በከረ 2:17:58 በመግባት 2ኛ ደረጃን ስትይዝ ሌላዋ ኢትዮጵያዊት ጎይቶም ገ/ስላሴ 20 ሰከንዶችን በመዘግየት 2:18:18 በመግባት 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

.
.

ፈለቀ ደምሴ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.