ተጠባቂው 187ኛው የማንቹሪያን ደርቢ።
▪️ ሁለቱ ቡድኖች መሀከል ያለው የነጥብ ልዩነት 19 መሆኑ እና ፖርቹጋላዊውን አጥቂ ክሪስቲያኖ ሮናልዶን ዶ ሳንቶስ አቪዬሮን በጉዳት ምክንያት አለማሰለፋቸውን ቀያዮቹ ላይ በመንፈስም በአካላዊ እንቅስቃሴም እንዳይጎዱ ያሰጋ ጉዳይ ነበር። በአንፃሩ ፔፕ ጋርዲዮላ ማንቸስተር ዩናይትድን በአሰልጣኝነት በገጠመባቸው ያለፉት 4 ጨዋታዎች በሜዳው ሽንፈትን ማስተናገዱ እና ማንቸስተር ዩናይትድ ያለፉትን 3 ጨዋታዎች በኤቲሀድ ስቴዲየም ወይም ከሜዳቸው ውጪ ያደረጋቸውን የደርቢ ጨዋታዎች ማሸነፉ እንደ ጠንካራ ጎን ወስደው ዩናይትዶች ወደ ሜዳ ገብተዋል። ማንቸስተር ሲቲ በበኩላቸው የመሀል ተከላካያቸውን ሩበን ዲያዝን በጉዳት ማጣታቸው የተከላካይ ክፍተት እንዳይፈጥርባቸው በመስጋት ግን ደግሞ የደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ እንደመሆናቸው መጠን መሪነታቸውን ለማስጠበቅ ወደሜዳ ገብተዋል።
▪️ጨዋታው ከመጀመሩ ገና በ260 ሰከንድ በርናርዶ ሲልቫ 3ተጫዋቾችን ቀንሶ ወደ 16:50 የላከውን ኳስ ቤልጄማዊው ኮኮብ ኬቨን ዴብራይን ኳሷን ከመረብ ጋር አዋህዷታል። 50ኛ የፕሪሚየር ሊግ ጎሉም ሆና ተመዝግባለች።
▪️በመልሶ ማጥቃት መጫወትን ምርጫቸው አድርገው ሲንቀሳቀሱ የነበሩት ቀያዮቹ ከ17 ደቂቃ በኋላ ሙከራቸው ተሳክቶ በጄደን ሳንቾ አማካኝነት የአቻነቷን ግብ ማግኘት ችለዋል። ወደ ዶርትመንድ ከማቅናቱ በፊት የሲቲ ተጫዋች የነበረው ሳንቾ ደስታውን ከመግለፆ ሲቆጠብ ታይቷል።
▪️ማንቸስተር ሲቲዎች በተደጋጋሚ መሪነታቸውን ለመረከብ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል። በ27ኛው ደቂቃ አሁንም ጥበበኛው ቤልጂየማዊ ኬቨን ዴብራይን እርዳታ አጥቶ ሲንገላታ የነበረው ዴቪድ ዴኸያ መረብ ላይ 2ኛውን ግብ ከመረብ አሳርፏል። 51ኛ ጎሉንም ማስቆጠር ችሏል። በፕሪሚየር ሊጉ 50 እና ከዛ በላይ ጎሎችን በማስቆጠር ሮሜሉ ሉካኩ ፣ ኤደን ሀዛርድ ፣ ክሪስቲያን ቤንቴኬን በመከተል 4ኛው ቤልጂየማዊ ተጫዋች መሆን ችሏል።
▪️ለእረፍት ውሀ ሰማያዊዎቹ ማንቸስተር ሲቲዎች መሪነታቸውን አስጠብቀው ወተዋል። ከእረፍት መልስም ተጭነው የተጫወቱት ማንቸስተር ሲቲዎች በ67ኛው ደቂቃ ኬቨን ዴብራይን ከማዕዘን ያሻገረውን ኳስ ከሳጥኑ ውጪ በተጠንቀቅ ሲጠብቅ የነበረው አልጄሪያዊው ሪያድ ማህሬዝ አክርሮ የመታው ኳስ ለ3ኛ ጊዜ የዴቪድ ዴኸያን መረብ ጋር ተዋህዳለች።ማህሬዝ በሁሉም ጨዋታዎች 20 ጎሉን ነው ለማንቸስተር ሲቲ ማስቆጠር የቻለው።
▪️ከዚች ግብ በኋላ የማንቸስተር ዩናይትድ የማጥቃት የቁመና ፣ ቅርፆ እንዲሁም ተነሳሽነት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ተሟጦ ታይቷል። ከእረፍት መልስ ምንም የግብ ሙከራ ማድረግ ሲቲ ላይ ማድረግ አልቻለም። በጭማሪ ደቂቃዎች ላይ ይህ አልጄራዊ ለራሱ 2ኛ ለቡድኑ ደግሞ 4ኛ ግብ አስቆጥሮ ጨዋታው 4-1 በሆነ ሰፊ ውጤት ጨዋታው ተጠናቋል።
ሚካኤል ደጀኔ።