39ኛው የጃንሜዳ እና የመጀመሪያው የምስራቅ አፍሪካ ኢንተርናሽናል ሀገር-አቋራጭ ውድድር ተካሄደ።
39ኛው የጃንሜዳ ሀገር-አቋራጭ ውድድር በየሁለት አመቱ የሚካሄዱ ሲሆን ስኬታማ አትሌቶችም ያፈራ እንዲሁም አዲስ አትሌቶች ለማፍራት ሚያስችል ሁነኛ መድረክ ነው። ዋልታ ቴሌቪዥን ውድድሩን በቀጥታ ስርጭት በማስተላለፍ ይህ ውድድር ለአትሌቲክሱ ቤተሰብ ተደራሽ እንዲሆን ሚዲያዊ ሽፋን የሰጠ ብቸኛው ተቋም ነው። በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና የተሰጠው ይህ ውድድር ዘንድሮ ከምስራቅ አፍሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ 6 ሀገራት ተሳታፊ ሆነዋል። ውድድሩንም የእለቱ የክብር እንግዳ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ክቡር አቶ ቀጀላ መርዳሳ እንዲሁም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ዳቦ በመቁረስ የውድድሩን መጀመር አብስረዋል።
ውድድሩ በስድስት ምድቦች ተከፍለው ማለትም
▪️በሴቶች በ6 ኪሎ ሜትር ወጣት ሴቶች
በድብልቅ ዱላ ቅብብል ዘርፍ
▪️በሴቶች የአዋቂ 10 ኪሎ ሜትር ዘርፍ
▪️በ8 ኪሎ ሜትር የወጣት ወንዶች
▪️የ10 ኪሎ ሜትር አዋቂ ወንዶች
እንዲሁም
▪️በ8 ኪሎ ሜትር የድብልቅ ዱላ ቅብብል( ሚክስድ ሪሌ) በሁለቱም ፆታዎች ይካሄዳል። ውድድሩን በቀዳሚነት ላጠናቀቁ አትሌቶች የወርቅ ፣ ብር ፣ ነሀስ ሽልማቶች ይሰጣል። በተጨማሪም ከ1 እስከ 6ኛ ለሚወጡ አትሌቶች ከ 40,000 ብር ጀምሮ እስከ 10,000 ብር የገንዘብ ማበረታቻ ሽልማት የሚበረከት ይሆናል። በአዋቂዎች ዘርፍ ሽልማቱን ከፍ በማድረግ ከ50,000 ብር ጀምሮ የገንዘብ ሽልማት የሚበረከት ሲሆን በአጠቃላይ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ ቬትራንን ጨምሮ እስከ 840,000 መድቧል።
▪️በድብልቅ ዱላ ቅብብል (ሚክስድ ሪሌ) ዘርፍ
ኦሮሚያ ክልል በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ ኦሮሚያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።መብራት ሀይል 3ኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል።
▪️በወጣት ሴቶች 8ኪ.ሜ ዘርፍ
1ኛ ብርቱካን ወልዴ ከ ሲዳማ ቡና የወርቅ ሜዳሊያ እና 40,000 ብር
2ኛ መዲና ኢሳ ከ አማራ ክልል የብር ሜዳሊያ እና 20,000 ብር
3ኛ አሳየች አይቼው ከአማራ ክልል የነሀስ ሜዳሊያ እና 16,000 ብር
4ኛ አንቺንአሉ ደሴ ፌ/ማረሚያ 14,000
5ኛ አለምናት ዋለ ከአማራ ክልል 12,000
6ኛ መሠረት የሻነው ከአማራ ክልል 10,000 ብር ተሸላሚ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል።
▪️በሴቶች የአዋቂ 10 ኪሎሜትር ዘርፍ
1.ጌጤ አለማየሁ ከኦሮሚያ ክልል በቀዳሚነት ውድድሯን ስታጠናቅቅ።
2.ራሄል ዳንኤል ከኤርትራ 2ኛ ስትሆን
3.እቴነሽ አላምረው አማራ ክልል 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
ዘውዲቱ አደራው ከአማራ ክልል
ቡዙነሽ ጌታቸው ኦሮሚያ ክልል
አለሚቱ ታሪኩ ከ ኦሮሚያ ክልል ከ 4 እስከ 6 በመግባት ውድድራቸውን አጠናቀዋል።
▪️በወጣት ወንዶች 8 ኪ.ሜ ዘርፍ
1.መለሰ ብርሀን አማራ ፖሊስ
2.በሠከት ነጋ ደቡብ ፖሊስ
3.ጭምዴሳ ደበሌ ኦሮሚያ ክልል
4.በረከት ዘለቀ ከአማራ ክልል
5.ሌሊሳ አራርሶ ከ ኦሮሚያ ክልል
6.ገበየሁ በላይ ከአማራ ክልል በመሆን አጠናቀዋል።
በአዋቂ ወንዶች 10 ኪሎ ሜትር ብርቱ ፉክክር የታየበት ሲሆን
▪️በሪሁ አረጋዊ በአንደኝነት ውድድሩን አጠናቋል።
ከ2 አመት በፊት በ8 ኪሎ ሜትር ወጣቶች በሪሁ አረጋዊ ማሸነፉ ይታወሳል። ዘንድሮ ደግሞ በአዋቂዎች ዘርፍ በአንደኝነት ውድድሩን አጠናቋል።
▪️አንዱአምላክ በሪሁ 2ኛ ሲሆን ይህ አትሌት በ36ኛው የጃልሜዳ ሀገር አቋራጭ ውድድር 3ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል። እንዲሁም በህንድ ኒውዴልሂ የተካሄደው የማራቶን ውድድር ክብረ ወሰን ባለቤት ነው።
▪️አየለ ከበደ 3ኛ
▪️ድንቃለም አያሌው 4ኛ
▪️ፀጋዬ ኪዳኔ 5ኛ እንዲሁም
▪️ሞገስ ጦማይ 6ኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል።
▪️ከ50 አመት በላይ
አብደላ ሱሌማን 1ኛ
አያሌው እንዳለ 2ኛ
ንጋቱ አጋ 3ኛ
ተስፋዬ ጉታ 4ኛ
ሸለመው ወ/ሰንበት 5ኛ
ንጉሴ አደራ 6ኛ ሆነው ውድድራቸውን ሲያጠናቅቁ።
▪️ከ50 አመት በታች
ደሳለኝ ተገኝ
እሱባለው አስናቀ
ተስፋዬ ያያ
ገዛኸኝ ገብሬ
አድነው መኮንን
ዳንኤል ቀቤሎ ከ 1 እስከ 6 በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል።
በቡድን የዋንጫ አሸናፊዎች።
▪️በድብልቅ ሪሌ
1ኛ ኦሮሚያ ክልል
2ኛ ኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን
3ኛ ኢትዮ ኤሌትሪክ
▪️6ኪሜ ወጣት ሴቶች
1ኛ አማራ ክልል በ20 ነጥብ
2ኛ ኦሮሚያ ክልል በ74 ነጥብ
3ኛ ኦሮ/ፖሊስ በ117 ነጥብ
▪️8ኪሜ ወጣት ወንዶች
1ኛ አማራ ክልል በ29 ነጥብ
2ኛ ኦሮሚያ ክልል በ44 ነጥብ
▪️10 ኪሜ አዋቂ ሴቶች
1ኛ ኦሮሚያ ክልል በ20 ነጥብ
2ኛ አማራ ክልል በ30 ነጥብ
3ኛ ኢት/ኤሌትሪክ በ61 ነጥብ
▪️10 ኪሜ አዋቂ ወንዶች
1ኛ ኢት/ኤሌትሪክ በ22 ነጥብ
2ኛ አማራ ክልል በ39 ነጥብ
3ኛ መከላከያ በ66 ነጥብ በማጠናቀቅ የዋንጫ ተሸላሚ መሆን ችለዋል።
ፈለቀ ደምሴ።