የጃንሜዳ ውድድር እና ሀገር አቋራጭ የምስራቅ አፍሪካ ሀገር አቋራጭ ውድድር በአንድ መድረክ።

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን በየአመቱ የሚያካሄደው የካቲት 6/2014 ዓ.ም ለ39ኛ ጊዜ የሚካሄደውን የጃን ሜዳ ኢንተርናሽናል ውድድር እና ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደውና ኢትዮጵያ እንድታካሂድ እድሉን ያገኘችበት የምስራቅ አፍሪካ አገር አቋራጭ ውድድር ዙሪያ ጉርድ ሾላ በሚገኘው የፌደሬሽኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ በዛሬው ለት ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የፌዴሬሽኑ ተቀ/ም/ፕሬዝዳንት አትሌት ገዛኸኝ አበራ፣የፌዴሬሽኑ አቃቤ ንዋይና ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ዶ/ር በዛብህ ወልዴ፣ የፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ተወካይ አቶ ዮሀንስ እንግዳ እንዲሁም የህክምና ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አትሌት አሸብር ደምሴ በየተራ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

▪️የውድድሩ አላማ ለተተኪ አትሌቶች እድል መፍጠር ቀዳሚው ሲሆን ፣ አትሌቶች የስልጠና ዝግጅታቸውን በውድድር እንዲፈትሹ ማስቻል ሌላኛው አላማ ነው።

▪️የዘንድሮውን 39ኛ የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ውድድር ለየት የሚያደርገው የምስራቅ አፍሪካ አገራት የአገር አቋራጭ ውድድርን ኢትዮጵያ እንድታዘጋጅ መመረጧ ነው።

ኢትዮጵያን ጨምሮ አስር የአፍሪካ ሀገራት ከሚገኙበት የምስራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን አባላት ሁሉም የተጋበዙ ቢሆንም ከ አስሩ መሀከል አምስት ሀገራት እስካሁን በውድድሩ ለመሳተፍ ማረጋገጫ መስጠታቸው ታውቋል።

ውድድሩ እሁድ የካቲት 6/2014 ከማለዳው 1:00 ጀምሮ እስከ 6:00 ድረስ በጃንሜዳ የሚካሄድ ሲሆን በአካል መምጣት ለማይችሉ የአትሌቲክሱ ቤተሰቦች በየቤታቸው በዋልታ ቴሌቪዥን ሙሉ ዝግጅቱ በቀጥታ እንደሚተላለፍ ተረጋግጧል።

▪️ለዚህ ውድድር ማካሄጃ ፌዴሬሽኑ 2.5 ሚሊዮን ብር በላይ መመደቡን ፣ ከ840ሺ ብርጨበላይ ለአሸናፊዎች ሽልማት መዘጋጀቱን ፣ ከ180 በላይ የአትሌቲክሱ ባለሙያዎች በተለያዩ አደረጃጀቶች የሚሳተፉ  እንዲሁም አለምአቀፍ ፈቃድና እውቅና የተሰጣቸው የአትሌቲክስ ዳኞች ውድድሩን እንደሚመሩት ከመግለጫው ያገኘነው ማብራሪያ ያሳያል።

ፈለቀ ደምሴ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.