ኢትዮጵያዊያን የደመቁበት የካርልስሩ ውድድር።

▪️የወርቅ ደረጃ ከተሰጣቸው የ2022 የቤት ውስጥ የአለም አትሌቲክስ የአመቱ የመጀመሪያው የሆነው በጀርመን ካርልስሩህ  በተካሄደው ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ደምቀው አምሽተዋል።

▪️በወንዶች በ3000 ሜትር የ20 አመቱ ኢትዮጵያዊ በሩሁ አረጋዊ በአንደኝነት አጠናቋል። በአቶ መላኩ ሚሰለጥነው እና የመብራት ሀይል ክለብ ውጤት የሆነው በሩሁ ውድድሩን ለማጠናቀቅ የፈጀበት 7:26:20 የቤት ውስጥ አትሌቲክስ 5ኛው ፈጣኑ ሰአት እንዲሁም የግሉ ምርጥ ሰአት ሆኖ ተመዝግቦለታል። በዚህ ርቀት ለ 24 አመት ተይዞ የነበረውን የኬንያዊ ዳንኤል ኮማን 7:24:90 ሪከርድ 2 ሰከንድ በመዘግየት ለጥቂት ማሻሻል ሳይችል ቀርቷል።

▪️በሴቶች 1500 ሜትር ብርቱ ፉክክር ታይቶበታል። በ2014 የቤት ውስጥ አትሌቲክስ የብር ሜዳሊስቷ ኢትዮጵያዊቷ አክሱም ልምዷን እና የአጨራረስ ብቃት ተጠቅማ 4:02:12 የግሏን ምርጥ ሰአት በማስመዝገብ በአንደኝነት ውድድሯን ስታጠናቅ ሌላዋ ኢትዮጵያዊ ሂሩት መሸሻ አንገት ለአንገት ተናንቃ  4:02:14 በመግባት 2ኛ ሆና ስታጠናቅቅ የቶኪዮ ኦሎምፒክ 4ኛ ሆና ያጠናቀቀችው ፍሬወይኒ ሀይሉ የግሏን ምርጥ ሰአት በማስመዝገብ 4:02:14 በመግባት 3ኛ ሆና አጠናቃለች።

ፈለቀ ደምሴ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.