የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ አቶ ውበቱ አባተ የሰጡት ቁጣ አዘል ጋዜጣዊ መግለጫ።

በዛሬው እለት ከአፍሪካ ዋንጫው መልስ ስለ ቆይታቸው እንዲሁም ስለ ቡድኑ ጠቅላላ ሁኔታ በዛሬው እለት በእግርኳስ ፌዴሬሽን ፆህፈት-ቤት የሰጡትን ቃለ-ምልልሱን እንደሚከተለው ቀርቧል።

ይዘን የነበረው ቡድን አስተማማኝ ነበር።
▪️የኬፕቨርድ ጨዋታ ያሰብነውን ነገር እንዳናሳካ አድርጎናል። ግን በpossession (ኳስን በመቆጣጠር ረገድ) ያን ያክል ልዩነት አልነበረንም።

▪️ከምድብ ማለፍ እቅዳችን ነበር ግን አልተሳካም በተለይ የመጀመሪያው ጨዋታ ላይ የተፈጠሩት ነገሮች ቀሪዎቹ 2 ጨዋታዎች ላይ የራሱን አሻራ አሳርፎብናል።

▪️የትኛውንም ቡድን አንፈራም ግን እናከብራለን። ልጆቹ የቻሉትን ሞክረዋል።

▪️ የመከላከል ስህተት ነበረብን ደካማ እንቅስቃሴ ነበረን በተለይ በተለይ ከኳስ ውጪ ያለን እንቅስቃሴ ደካማ ሆኖ አይቼዋለሁ ማሻሻል አለብን ብለዋል።

▪️ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር እየተነጋገርክ ነው ሚባል ነገር አለ። እኔ ምንም የማውቀው ነገር የለም ከ rumor የዘለለ አይደለም ብለዋል።

▪️ጌታነህ ከበደ የቡርኪናፋሶው ጨዋታ ላይ ማልያ ተለዋውጧል ለሚለው ጥያቄ? አዎ ተለዋውጧል ከ አስቶን ቪላው ትራኦሬ ጋር ነው ማልያ የተቀያየረው ትራኦሬ ደግሞ ለደጋፊዎቹ ሰጥቶቷል ብለዋል።

▪️3 ተጨማሪ ተጫዋቾች ካፍ እንድናካት ፈቅዶ 28 ተጫዋች መርጫለሁ። 40ም መሆን ይችል ነበር ግን ከአቅም እና ሎጅስቲክ ጉዳይ ጋር ተያይዞ ነው።

▪️ሽሜ ጉዳት አልነበረበትም። ከሱዳን ጋር በካሜሮን ያደረግነውን የወዳጅነት ጨዋታ ተጫውቷል። ኮቪድ ግን ስለነበረበት ሶስቱም ጨዋታዎች አልፈውታል።

▪️የካሜሩን አቻ ያደረጉት የመጀመሪያ ጎል ቫር ነው። 3ኛው ጎል ግን መስኡድ ላይ የተሰራው ጥፋት ሊያነጋግረን ይችል ይሆናል።

▪️ በአምላክ ደውሎልኝ ልጆችህ በዚ ደረጃ ለምን ዝም ይላሉ መጠየቅ ያለባቸውን መጠየቅ አለባቸው። ይህንን መንገር መቻል አለብህ ብሎኛል ብሏል። ማንም ያላየውን ነገር ዳዋ አይቶ ለዳኛው በማሳወቁ የፍፁም ቅጣት ምት ማግኘት ችለናል ብለዋል።

▪️ኮሞሮስ እና ጋምቢያ ትንሽ ሀገር ወይም የመጀመሪያ ተሳትፎአቸው ስለሆነ ሊሆን ይችላል ግን ምንማርበት ነገር አለ።

▪️ስትሄዱ በይፋ ስትመጡ ተደብቃችሁ ነው ለተባለው ጥያቄ. ስንሄድም ስንመጣም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው ብለዋል። ቲክ ቶክ ላይ እንዳየነው ህዝባችን ድንጋይ ይዘው አልጠበቁንም ብሄራዊ ቡድኑ የሁላችንም እንደመሆኑ መጠን ተደብቀን ምንመጣበት ምንም ምክንያት የለም በዚህ ደረጃ ለማብጠልጠል ባይሞከር ጥሩ ነበር አየር መንገዱ ላይ ተገኝተህ ይሄን ጥያቄ መጠየቅ ትችል ነበር ..ብሄራዊ ቡድን ማሰልጠን ትልቅ ነገር ነው። ትልቅ ክብር ነው። ቅ/ጊዮርጊስ ማሰልጠን የተሻለ ነገር እጠቀምበት ሊሆን ይችላል። እስከ ግማሽ ሚሊዮን ማገኝበትም ነገር ነበር ግን ያን ሁሉ ትቼ ነው ብሄራዊ ቡድኑን እያሰለጠንኩ ያለሁት ብለዋል።

▪️ኮንትራቴ እስከ መስከረም 30 ይቆያል እስከ እዛ ድረስ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ነኝ።
መጋቢት ወር ላይ ላይ የወዳጅነት ጨዋታ አለን ለሱ እየተዘጋጀን ነው ትኩረታችን እሱ ላይ ነው።
▪️ለወደፊቱ ፈጣሪ ነው የሚያውቀው ግን እኔ ብቀጥልም ፣ ባልቀጥልም መልካሙን ሁሉ ለብሄራዊ ቡድኑ እምመኝ ሰው ነኝ ግን በነበረኝ ጊዜ ብሄራዊ ቡድኑ ትልቅ መድረክ ላይ ጥሩ ውጤት ማምጣት እንደሚችል ተስፋዎች እንዳሉት ተመልክቻለሁ ሲሉ መልሰዋል።

▪️ ስለ ውጭ ተጫዋቾች በድጋሜ ተነስቷል።
አቶ ውበቱ አባተ ግን በ13 ቀን ውስጥ የውጭ ዜጎችን ከቡድኑ ጋር ማካተት ቢከብድም ግን ብቃታቸውን ለማየት ሞክሬዋለሁ ብለዋል። ቢሰራበት እና ቢካተቱ ግን ለብሄራዊ ቡድኑ ጠቀሜታ እንዳላቸው አያጠያይቅም ሲሉም አክለዋል።
▪️አቶ ባህሩ በበኩላቸው የፓስፖርት ጉዳይ (ጥምር ዜግነት) ስለማይፈቅድ ነው ብለዋል። ከዚ ቀደም የሱፍ ሳላ ተጫውተዋል ሚባል ነገር ይነሳል ግን ያኔ የአመራር እና የአተገባበር ችግር ስለነበር ነው ሲሉም አክለዋል።

ጋዜጠኞች ለምን አልሄዱም? ለሚለው ጥያቄ  ባህሩ ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል።
▪️ሲሳይ አድርሴ ፕሮሞሽን ጋር ስፖንሰር አድራጊ ፈላጊዎች ፈልጎ 25 ጋዜጠኞችን እወስዳለሁ ብሎን (late hour) ባለቀ ሰአት ላይ እንደማይችል ነግሮናል። እንደ እግርኳስ ፌዴሬሽን ግን የሰጠውን ምክንያት አልተቀበልነውም እኛም ምንመ ማድረግ አልቻልንም ብሏል።
እንደ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የ2 አመት ኮንትራት ነው የሰጠነው። ለአፍሪካ ዋንጫ አሳልፎናል እናመሰግነዋለን።ኮንትራቱም እስከሚጠናቀቅ ድረስ የኛ አሰልጣኝ ሆኖ ይቀጥላል ሲሉ ንግግራቸውን ቋጭተዋል።

ሚካኤል ደጀኔ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.