የአየርላንዱ ሀገር አቋራጭ ውድድር።

▪️አለምአቀፉ የሰሜን አየርላንድ ሀገር አቋራጭ ውድድር በደንድላንድ ከተማ ተካሂዷል። የመጀመሪያው የሰሜን አየርላንድ ኢንተርናሽናል ሀገር-አቋራጭ ውድድር እ.ኤ.አ በ1977 በማለስክ ግዛት እንደተካሄደ የታሪክ ምንጮች ያሳያሉ። ከ 600 በላይ የሆኑ አትሌቶች የተሳተፉበት ይህ ውድድር ዘንድሮ ሲካሄድ ለ 44ኛ ጊዜ ነው።

▪️በሴቶች በተካሄደው የ8 ኪሎሜትር ሩጫ ኬንያዊቷ ሄለን ኦቢሪ 26:44 በመግባት አሸናፊ ሆናለች የሀገር አቋራጭ ውድድሮች አዲስ ያልሆነችው ሄለን ኦቢሪ በአየርላንድ ስትሮጥ የመጀመሪያዋ ነው። “ፈታኝ ነበር ግን ማሸነፍ ችያለሁ ብላለች። የ 2ጊዜ የአለም 5000 ሜትር ሻምፒዮኗ ሄለን ኦቢሪ። የፈረንጆቹ አዲስ አመት 2022 ከገባ በኋላ የመጀመሪያ ድሏ ሲሆን ከፊቷ የአለም ሻምፒዮና እንዲሁም ዳይመንድ ሊግ እንደሚጠብቃት ገልፃ ከአሰልጣኟ ጋር በመሆን ለሷ ጥሩ እና ምቹ የሆነው ውድድር ላይ እንደምትዘጋጅ ለ ቢቢሲ ስፖርት ሀሳቧን አጋርታለች።ሰሜን አየርላንዳዊቷ ሀና ኢርዊን 2ኛ ስትሆን ከ 3 ሰከንድ በኋላ ስኮትላንዳዊቷ ምሀሪ ማክሌን 3ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሯን ቋጭታለች።በኦሎምፒክ እንዲሁም በአትሌቲክስ የሩጫ ውድድሮች ላይ አንድ የአየርላንድ ወይም ለስኮትላንድ ሀገር ሚሮጥ አትሌት ግሬት ብሪቴን( ታላቋ እንግሊዝ) እንጂ በሀገሩ እንደማይመዘገብለት ይታወቃል። በዚህም መሰረት ከ 2 እስከ 4 የወጡ አትሌቶች ውጤታቸው በግሬት ብሪቴን ስም ሚመዘገብ ይሆናል።

▪️በወንዶች የ10 ኪሎሜትር ሩጫ ተካሂዷል። ዛክ ▪️መሀመድ ከእንግሊዝ 29:49 በመግባት ቀዳሚ ነው።
▪️ጣልያናዊው ሊያስ አውታኒ 29:56 በመግባት 2ኛ ሲሆን ሌላው እንግሊዛዊ ስቱዋርድ ማካለም 30:03 በመግባት 3ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

ፈለቀ ደምሴ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.