ወቅቱ ያደበዘዘው 21ኛው የኢትዮጵያ ታላቁ ሩጫ።

21ኛው የኢትዮጵያ ታላቁ ሩጫ።

በየአመቱ በሀገራችን የሚካሄደው እና በርካታ ኢትዮጵያዊያን እና የውጭ ዜጎች ሚሳተፉበት የቶታል ኢነርጂ ታላቁ ሩጫ ዛሬ ተካሂዷል።
ለ21ኛ ጊዜ የተካሄደው ይህ ታላቁ ሩጫ ዘንድሮ ለየት የሚያደርገው የሀገር ጥሪን ተቀብለው ወደ ሀገራቸው የገቡ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በውድድሩ መካፈላቸው ሲሆን ሀገራችን ላይ ባለው ጦርነት እና በኮቪድ ምክኒያት  በርካታ የውጭ ተሳታፊዎች ያልተገኙበትና ከሌላው ግዜ የቀዘቀዘ ነበር ።

👉 የዘንድሮው ታላቁ ሩጫ ለ21ኛ ጊዜ የተደረገ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው በ1994 ህዳር 16 ቀን ነበር።

በሻለቃ አትሌት ሀይሌ ገ/ስላሴ አማካኝነት ውድድሩ ተመስርቶ የመጀመሪያው አሸናፊም እንደነበር ይታወሳል። ከዛን ጊዜ አንስቶ ስለሺ ስህን እንዲሁም ገ/እግዛብሄር ገ/ማርያምን ጨምሮ የተለያዩ አትሌቶች በውድድሩ አሸናፊዎች ነበሩ።

የተሳታፊዎች ደረጃም ቁጥራቸው ከአመት አመት እየጨመረ ሄዶ ከ40,000 በላይ የሆኑ ተሳታፊዎች በማስተናድ በአፍሪካ ትልቁ የስፖርት መድረክ መባል ችሏል።

አምና በኮቪድ ወረርሽኝ ተሳታፊዎቹን ወደ 12,000 የተቀነሰበት ታላቁ ሩጫ ዘንድሮ ቁጥሩ ተሻሽሎ 25 ሺ ተሳታፊዎችን አስተናግዷል።

▪️10 ኪሎሜትሮችን የሚሸፍነው ይህ ሩጫ መነሻውም መድረሻውም መስቀል አደባባይ ሲሆን ከኮቪድ ወረርሽኝ አሁንም ሀገራችን ሙሉ ለሙሉ ነፃ አይደለችምና ሩጫው በ ሶስት ማዕበል ተከፍሎ ማለትም የመጀመሪያ አረንጋዴ ለባሾች ሲጀምሩ
በቀጣይ ቢጫ ለባሾችና ቀይ ለበሾች ተከታትለው  ጀምረዋል ከ25 ሺዎቹ ተሳታፊ ሯጮች አስቀድሞ ፕሮፌሽናል የሆኑ ሯጮች 2:00 ላይ ውድድሩን ጀምረዋል። 4 የሻወር ስቴሽኖች እና በየኪሎሜትሩ ሯጮች ስንት ኪሎሜትር እንደሮጡ እንዲሁም እንደሚቀራቸው የሚያሳይ ምልክቶችም ነበሩ ።

በየቦታው የውሀ አቅርቦት እንዲሁም ሯጮችን የሚያበረታቱ ሙዚቃዎች በስፒከር ተከፍተዋል። ይህ ታላቁ ሩጫ የተለያዩ አንድምታዎች ያሉት ሲሆን ከበጎ አድራጎት ጋር በተያያዘ ባሳለፍነው አመት ብቻ 1.6 ሚሊዮን ብር የተሰበሰበ ሲሆን ዘንድሮም ወደ 1.7 ሚሊዮን ብር ይሰበስባሉ ተብለው ይጠበቃል።

👉በሴቶች 1ኛ ደረጃ ይዛ ያጠናቀቀችው ያለምዘርፍ የኋላው ከ 2 አመት በፊት በተካሄደው 19ኛው ታላቁ ሩጫ ላይ 28:23 በመግባት 1ኛ መውጣቷ ይታወሳል። ከውድድሩ ላይ አስቀድማ ቃል በገባችው መሠረት ውድድሩን ስታሸንፍ ሜዳልያዋን ለጋናዊቷ ዶክተር ሴተር ኖር ጊቤ አበርክታለች።

21ኛው የኢትዮጵያ ታላቁ ሩጫ

👉 2:00 ሲል የፕሮፌሽናል አትሌቶች ሩጫ ተጀምሯል።

👉 2:10 ሲል 10 ኪሎሜትር የሚሸፍነው ታላቁ ሩጫ አረንጓዴ ፣ ቢጫ ፣ ቀይ የለበሱ በ25000 ተሳታፊዎች አሸብርቆ  ተጀምሯል።

👉2:18 የ2014 የቶታል ኤነርጂስ የታላቁ ሩጫ የወንዶች ሩጫ አስደናቂ አጨራረስ እና ትንቅንቅ ታይቶበታል።

👉 2:23 ኢትዮጵያን አትሌቶች ተከታትለው 1ኛ እና 2ኛ ገብተዋል። ኬንያዊው አትሌት 6ኛ ሆኖ አጠናቋል።

👉 2:25 በሴቶችም በከፍተኛ ፉክክር የቀጠለ ሲሆን ግርማዊት ገ/እግዛቤር እየመራች ነበር ሆኖም በመጨረሻ ሁለተኛ ሆና አጠናቃለች።

▪️የወንዶች አጠቃላይ ውጤት

 

1. ገመቹ ዲዳ ከ ኢትዮ ኤሌትሪክ 27:22.9
2.ጌታነህ ሞላ ከ መከላከያ 27:23.4

3.ቦኪ ድሪባ ከ ኤሊት ስፖርት ማኔጅመንት 27:23.6
4.ሞገስ ቱሜ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ 27:29.9
5.ጌታቸው ማስረሻ ሸ አማራ አትሌቲክስ 27:31.4
6.ኮርኒየስ ኪቤት ኬንያዊ አትሌት 27:37.9
7.አንታየሁ ዳኛቸው አሰልጣኝ 27:41.6
8.ሰለሞን በሪሁን ኢትዮ ኤሌትሪክ 27:53.6
9.አሸናፊ ኪሮስ ከ ቮላሬ ስፖርት 27:58.2

👉የሴቶች አጠቃላይ ውጤት
1.ያለምዘርፍ የኋላው 30:14.2
2.ግርማዊት ገ/እግዛብሄር 30:26.9

3.መልከናት ውዱ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 30:41.9
4.ጌቴ አለማየሁ በግል 31:03.2
5.ቦንሰና ሙላቴ በግል 31:14.4
6.ሀዊ ፈይሳ መከላከያ 31:15.5
7.ብርቱካን ወልዴ ሲዳማ ቡና 31:19.9
8.አንቺንአሉ ደሴ ከዲሞንዳ አትሌቲክስ 31:35.4
9. መብራት ግደይ ከ ኮልፌ ቀራኒዮ አትሌቲክስ 31:29
10.አይናዲስ ተሾመ ኢትዮ ኤሌትሪክ 31:46.7
1ኛ ለወጣ አትሌት 100,000
2ኛ ለወጣ አትሌት 30,000
እንዲሁም 3ኛ ለወጣ አትሌት 12,000 ብር ተበርክቶላቸዋል ።

👉3:24 የሽልማት ስነ-ስርአት ተከናውኗል ።

👉ሸልማቱን ለአሸናፊዎች ያበረከቱት አምባሳደር መስፍን ቸርነት በባህልና ስፖርት ሚኒስትር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ፣ አትሌት ገዛኸኝ አበራ ፣ ብርሀኔ አደሬ፣ እንዲሁም ሀይሌ ገ/ስላሴ ናቸው።

በወንዶች ጃፋር ጀማል 1500 ኪሎ ሜትር በ 100 ቀናት ውስጥ እንዲሁም በሴቶች የግሌ እሸቱ በ100 ቀን 950 ኪሎሜትር በመሮጥ ለጥሩ ስራቸው እና ለአርአያናታቸው

ከሶፊ ማልት ማኔጀር እና ከአትሌት መሠረት ደፋር እጅ ሽልማታቸውን ተቀብለዋል።

 

 

👉ዘቢባ ሚፍታ በኢትዮጵያ አየርመንገድ ማርኬቲንግ ዳይሬክተር ሲሆኑ

በውድድሩ ከተሳተፉ አምባሳደሮች ውስጥ እሸናፊ ለሆኑት የቤልጂየሙ ፎንሱአስ ዱቧ ሽልማት አበርክተዋል።

👉10:05 አትሌት ገዛኸኝ አበራ ከ 50 አመት በላይ ለሆኑ እና ውድድራቸውን ላጠናቀቁ ተሳታፊዎች

1ኛ አብደላ ሱሌማን

2ኛ ንጋቱ ነጋ
3ኛ ተስፋዬ ጉታ ሽልማት አበርክቷል ።

በመጨረሻም የዘንድሮው የቶታል ኢነርጂ ታላቁ ሩጫ
እስከ 5.30 ዘግይተው የገቡ ተሳታፊዎችን በመጠበቅ
ተጠናቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.