የዘንድሮውን “THE BEST” ሽልማት አሸናፊ ማ ይሆን?

ለ6ኛ ጊዜ የሚከናወነው እና በ FIFA አዘጋጅነት የሚካሄደው “THE BEST” Football award በአመት ውስጥ ምርጥ ብቃታቸውን እና እንቅስቃሴ ያሳዩ ተጫዋች እና አሰልጣኝ ሚበረከት ሽልማት ነው። በሁለቱም ፆታዎች ሽልማቱ የሚበረከት ሲሆን የመጨረሻ እጩዎች ታውቀዋል።

▪️በሴት ተጫዋች ዘርፍ የBallon’dor አሸናፊዋ የባርሴሎናዋ አሌክሲያ ፑቴላስ ከቡድን አጋሯ ጄኔፈር ሄርሞሶ እና የቼልሲዋ የፊት መስመር ተጫዋች ሳም ኬር ጋር ተፋጣለች። የማንቸስተር ሲቲ እና የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች የሆነችው ሉሲ ብሮንዝ እንዲሁም የኔዘርላንድ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች እና የመድፈኞቹ አጥቂ የሆነችው ቪቪያን ሚዴማ ተፎካካሪ የነበሩ ቢሆንም የመጨረሻ እጩ ዝርዝር ላይ ግን ስማቸውን ማስፈር አልቻሉም።

▪️በወንዶች የተጫዋች ዘርፍ 7ኛ ባሎንዶሩን ከፍ አድርጎ ያነሳው ሊዮኔል ሜሲ አሁንም የዋንጫ ቁምሳጥኖቹ ላይ ይህን ዋንጫ ማስፈር ቢፈልግም ጠንካራ ፉክክር ከሮበርት ሌዋንዶውስኪ እና ግብፃዊው ሞሀመድ ሳላህ ይጠብቀዋል።

ሜሲ ባርሴሎናን ከለቀቀ በኋላ በ ፓሪስ ሴንት ጀርሜ ጥሩ ጊዜ ለማሳለፍ እየተቸገረ ሚገኝ ሲሆን በአንፃሩ ሌዋንዶውስኪ ለ 49 አመት በጀርድ ሙለር ተይዞ የነበረውን በአንድ አመት ውስጥ ብዙ ጎል የማስቆጠር ሪከርድን 46 ጎሎች በማስቆጠር መስበሩ ይታወሳል በባሎንዶር ሌዋንዶውስኪ አለማሸነፉ አነጋጋሪ እንደነበር ይታወሳል ይህን ሽልማት ግን ለመውሰድ ቅድመ-ግምት ተሰቶታል።

▪️በሴቶች የአሰልጣኝ ዘርፍ የካቻምናዋ አሸናፊ ሳሪና ዊዬገን የኔዘርላንድ ሴቶች ብሄራዊ ቡድንን በአውሮፓ ዋንጫ እንዲያሸንፍ ማድረጎ ይታወቃል። አሁን በቅርቡ ደግሞ የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድንን እያሰለጠነች ትገኛለች።
▪️እንዲሁም የባርሴሎናው አሰልጣኝ ልዊስ ኮርቴዝ የባርሴሎና ሴቶች ክለብ የቼልሲ ሴቶች ክለብን በሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ 4-0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፈው ዋንጫ እንዲያነሱ ከማስቻሉ በላይ የኮፓ ዴል ሬ ዋንጫ እንዲያሳኩ አስችሏል።

▪️የቼልሲዋ አሰልጣኝ ኤማ ሄይስ የመጨረሻዋ እጩ ስትሆን የእንግሊዝ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ መባሏ እና የቼልሲ ቡድንን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ትልቁ መድረክ የሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ እንዲያልፍ ማድረግ ችላለች።

▪️በወንዶች አሰልጣኝ ዘርፍ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዘንድሮም ብዙ እጩዎችን ማስመረጡን ቀጥሎበታል።

▪️ፔፕ ጋርዲዎላ አንዱ እጩ ሲሆን ማንቸስተር ሲቲ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ከፍ አድርጎ እንዲያነሳና ለሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ እንዲያልፍ አስተዋጽኦ ቀላል አይደለም።

▪️ቶማስ ቱኸል ሌላው እጩ ነው ይህ ጀርመናዊ አሰልጣኝከዛሬ አመት በፊት  በጥር ወር ቡድኑን ከፍራንክ ላምፓርድ ከተረከበ በኋላ ቡድኑ ባሳየው ቅፅበታዊ ለውጥ የሻምፒዮንስ ሊግ ከፍ አድርገው እንዲያኘሱ አስችለዋል።

▪️ የመጨረሻው እጩ ሮቤርቶ ማንሲኒ ሲሆኑ አዙሪዎቹ እየተባሉ ሚጠሩትን የጣልያን ብሄራዊ ቡድንን በፍፃሜው የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድንን በመርታት የ2020 የአውሮፓ ዋንጫን እንዲያነሱ ማስቻሉ ይታወሳል።

▪️የፑሽካሽ የአመቱ ምርጥ ግብ ይህ ዘርፍ በአመቱ ውስጥ ከመረብ ከተዋሀዱ ምርጥ እና ድንቅ ግቦች ተመርጦ ሚሸለምበት ዘርፍ ሲሆን

▪️ኤሪክ ላሜላ አንዱ እጩ ሲሆን አምና በኤምሬትስ ስታዲየም ቡድኑ ከ አርሰናል ጋር ባደረገው ጨዋታ በተለምዶው ራቦና እየተባለ በሚጠራው ቄንጠኛ አመታት ግብ ማስቆጠሩ ይታወሳል።

▪️ሌላው እጩ የፓርቶው የሜህዲ ታሬሚ ግብ ነው ይህች ግብ ቼልሲ ላይ በሻምፒዮንስ ሊጉ የተቆጠረች ግብ ናት አክሮባቲክ በሆነ መንገድ ሜንዲ ላይ ይህ ግብ ሊቆጠር ችሏል።

▪️የመጨረሻው እጩ ፓትሪክ ሺክ ሲሆን ይህ ቼካዊ በአውሮፓ ዋንጫ ሀገሩ ቼክ ከ ስኮትላንድ ጋር ባደረገችው ጨዋታ ከረጅም ርቀት የመታው ኳስ በተለምዶው lob እየተባለ ሚጠራውን አመታት ተጠቅሞ ያስቆጠራት ግብ እጩ ዝርዝር ውስጥ ተካታለች።

ሚካኤል ደጀኔ

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.