የዋልያዎቹ አጣብቂኝ ጉዞ።

በትላንትናው እለት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የምድብ 2ኛ ጨዋታውን ከአዘጋጇ ካሜሮን ጋር  ምሽት 1:00 ላይ በያውንዴ ስታዲየም አከናውኗል። ብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ አቶ ውበቱ አባተ ከዚ በፊት የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታዋን ከኬፕቨርድ ጋር ሲያደርግ ከተጠቀመባቸው ተጫዋቾች ለውጥ አድርጎ ነበር ጨዋታውን የጀመረው ጌታነህ ከበደ በዳዋ ሆቴሳ እንዲሁም መስኡድ መሀመድ ወደ ቋሚ አሰላለፉ መምጣት ችሏል።እንዲሁም ተከላካዩ  ያሬድ ባየህ ቀይ ካርድ በማየቱ ምኞት ደበበ እሱን ተክቶ ወደ ሜዳ ገብተዋል።

▪️ጨዋታው በጥሩ ሁኔታ የጀመረው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጨዋታው በተጀመረ በ 4ኛው ደቂቃ ላይ ከቀኝ መስመር ላይ ከአማኑኤል ገ/ሚካኤል የተሻገረለትን ኳስ በቀላሉ በማስቆጠር ኢትዮጵያ ካሜሮንን 1-0 መምራት ጀመረች።

መሪነቷ ግን ለ 4 ደቂቃዎች ብቻ ነው መቆየት የቻለው 8ኛው ደቂቃ ላይ በቀኝ መስመር ላይ ከኮሊንስ ፋይ የተሻገረውን ኳስ ሱሌማን ሀሚድ ከኋላ የተወውን ቦታ ቶኮ ኤካምቢ ነፃ ሆኖ በሚገባ በመጠቀም ኳሷን በጭንቅላቱ ከመረብ ጋር አዋህዷል።

ይህች ጎል ከተቆጠረች በኋላ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በአማኑኤል ገ/ሚካኤል እንዲሁም በሱራፌል ዳኛቸው ሙከራዎችን ማድረግ ችለው ነበር። ግን የአያክሱ ግብ ጠባቂ አንድሬ ኦናና ሚቀመስ  አልሆነም። በመከላከሉ ረገድም ቢሆን የክንፍ ተጫዋቾቹ ድክመት ቢታይም መሀል ላይ አስቻለው ታመነ እና ምኞት ደበበ ጥምረት ይበል የሚያሰኝ ነበር።የመጀመሪያው አጋማሽም በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ።

ከእረፍት መልስ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ቢጫ ካርድ ያየውን ሱራፌል ዳኛቸውን አስወጥተው ፍሬው ሰለሞንን ተክተው አስገብተዋል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የመጨረሻው መጀመሪያም እዚ ጋር ይጀምራል ቅያሪው ተገቢ ቢሆንም ፍሬው ሰለሞን ተተክቶ ገብቶ ለቡድኑ ምን አደረገ ሚለው ነገር ትልቅ ጥያቄ ፈጥሯል።
ሁለተኛው አጋማሽ ከተጀመረ 8 ደቂቃ ካለፈው በኋላ በረመዳን የሱፍ በኩል ያለውን ክፍተት ተጠቅሞ አሁንም ኮሊንስ ፋይ ያሻገረውን ኳስ ግዙፉ አጥቂ ቪንሰንት አቡበከር በጭንቅላት በመግጨት ቡድኑን 53ኛው ደቂቃ ላይ መሪ አደረገ። አስቻለው ታመነ ሙሉ ለሙሉ ተጫዋቹን ማርክ ባለማድረጉ ጎሉን እንድናስተናግድ አድርጎናል።

ካሜሮን መሪነቱን ያጠናከረችበትን ግብ ከ 2 ደቂቃ በኋላ አስቆጥራለች። መከላከል ትራንዚሽን ላይ ሙሉለሙሉ በሚባል ደረጃ ድክመት ታይቶብናል። ቪንሰንት አቡበከርም ለሀገሩ ባደረጋቸው 79 ጨዋታዎች 29ኛው ግብ ሆና ተመዝግባለታለች።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በጣም ተዳክሞ ታይቷል።በመከላከሉም በማጥቃቱም ረገድ  ከእረፍት መልስ እጅግ ደካማ ሆኖ ታይቷል። 67ኛው ደቂቃ ላይ የሊዮን የግራ ክንፍ አጥቂ መስመር ላይ ሚጫወተው ካርል ቶኮ ኤካምቢ በአስደናቂ አጨራረስ 3 የኢትዮጵያ ተከላካዮችን አተሪራምሶ ለካሜሮን 4ኛውን ለሱ ደግሞ በምሽቱ 2ኛውን ግብ አስቆጥሯል።ውጤቱም 4-1 በሆነ ሰፊ ውጤት ተጠናቋል።

በጎል ድርቅ ተመቶ የነበረው የ2021 የአፍሪካ ዋንጫ በትላንትናው ጨዋታ ጎሎች ዘንቦበታል። ውጤቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጥሎ ማለፉን የመቀላቀል እድሉ ተመናምኗል ማለት ይቻላል። ይህ ጨዋታ ከመጠናቀቁ በኋላ የቡርኪና ፋሶው እና የኬፕቨርድ ጨዋታ ቀጥሏል። ቡርኪናፋሶ 1-0 በሆነ ውጤት አሸንፋለች ነጥቧን 3 በማድረስ 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ኢትዮጵያም የምድብ የመጨረሻ ጨዋታውን ከቡርኪናፋሶው ጋር የፊታችን ሰኞ ያካሄዳል።

ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ አስተያየት እንዲሁም ከ ጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄ ማብራሪያ እና ምላሽ ሰተዋል።

” ከእረፍት መልስ ቡድኑ ደክሞ መታየቱን አምኗል። 3ኛው ጎል ላይ ግን ጥያቄ አነሳለሁ የሐሀል ሜዳው ላይ ኳሱን ስንነጠቀ ጥፋት ተሰርቶብን ነበር በዛ ምክንያት ነው የተሸነፍነው እያልኩ ግን አይደለም።
በዛ ላይ በጣም ልምድ ካለው ጠንካራ ቡድን ጋር ነው የተጫወትነው ስለዚህ ይህ ለኛ ከባድ ነገር ነው። እነሱም ማሸነፍ ይገባቸው ነበር ብለዋል”።

🗣 ከእረፍት መልስ ቡድንህ እየደከመ ይታያል ምክንያቱ ምንድን ነው? ተብሎም ተጠይቆ ነበር።

“እሱም የልምድ ማነስ እና ትልቅ ደረጃ ትልቅ መድረክ ላይ የመጫወት ልምድ ያላቸው ተጫዋቾች የሉንም ምክንያቱ እሱ ነው ብለው መልሰዋል”።

▪️ የጨዋታ ተንታኝ የነበረው የጋናው አንጋፋ አጥቂ አሳሞ አጂያን ስለ ኢትዮጵያ እንዲህ ብሏል ”ከጋና ጋር ሲጫወቱ ጨዋታውን ተመልክቼው ነበር ኳስ በጣም ይዘው ነበር በዛሬው ጨዋታ ግን ተመሳሳይ ነገር ማድረግ አልቻሉም።ከእረፍት በፊት ያልጠበቅነው ጥሩ እንቅስቀሴ ቢያሳዩም ትንሽ ቡድን እንደመሆናቸው መጠን ሳይኮሎጂካሊ ተበልጠው ተሸንፈዋል ግን ውጤቱ በዚ መልኩ እንደሚጠናቀቅ ታውቆኝ ነበር” ብሏል።

▪️የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከ8 አመት በኋላም  ከደካማ እንቅስቃሴ ጋር ታጅቦ ከምድብ ማለፍ እንኳን ሳይሆን ነጥብ እንኳን ማግኘት ሳይችል ወደ ሀገሩ ሊሸኝ ሻንጣ እያሰናዳ ይገኛል። ይህን ውድድር ለማድረግ ወደ ካሜሮን ቀድሞ ያቀና የመጀመሪያው ብሄራዊ ቡድን ቢሆንም ለመሸኘትም የመጀመሪያው ሊሆን ከጫፍ ደርሷል።በጣም ትልቅ የቤት ስራ በእግርኳስ ፌዴሬሽኑ መሰራትም ይገባዋል።

ከዘመናዊ እግርኳሱ ጋር አብረው ሊሄዱ ሚችሉ የእግርኳስ መሰረታዊ ቴክኒኮች መንፀባረቅ ይገባቸዋል። ታዳጊዎች እና ተተኪዎችን ማፍራት ላይ ስር ነቀል ለውጥ ያስፈልጋል ብለን እንደ ኢትዮጵያንስ ስፖርት እናምናለን።

ሚካኤል ደጀኔ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.