ኢትዮጵያውቷ አትሌት በስፔን ማድሪድ ከተማ የተካሄደው የ10 ኪሎሜትር ሩጫ አሸናፊ ሆነች።
▪️ይህ ውድድር እኤአ ከ1964 ጀምሮ ሲካሄደ የነበረ ታሪካዊ ውድድር ሲሆን በ2012 እስከ 40,000 ተሳታፊዎችን ያካተተ ውድድር ነበር።
▪️ኢትዮጵያዊቷ ደጊቱ አዝመራው በማድሪድ ከተማ san silvestre, vallecana የተካሄደውን የጎዳና ላይ የ10 ኪሎሜትር ሩጫ አሸናፊ መሆን ችላለች። ደጊቱ በለንደን ማራቶን ጥቅምት ወር ላይ 2:17:58 ከገባች በኋላ ሌላ ያሸነፈችበት መድረክ ሆኖላታል።
▪️ 2 ጊዜ የ 5,000 ሜትር ሻምፒዮኗ ኬንያዊቷ ሄለን ኦቢሪ ውድድሩ ሊካሄድ አንድ ቀን ሲቀረው ኮቪድ 19 ፖዘቲቭ ሆና በመገኘቷ ከውድድሩ ውጪ ሆናለች።
▪️ደጊቱ አዝመራው ውድድሩን ለመጨረስ 30:26 የፈጀባት ሲሆን 3ኛ ፈጣን ሰአቷ ሆኖ ተመዝግቦላታል። ኬንያዊቷ ጄቢቶክ በቅርቡ በስፔን ቫንታ ዴ ባኖስ በተደረገው ሀገር-አቋራጭ አሸናፊ እንደነበረች ይታወሳል። እዚ ውድድር ላይ ደጊቱን 18 ሰከንዶችን በመዘግየት 2ኛ ሆኖ አጠናቀዋል። እእስራኤላዊቷ ሎና ሳልፔተር 3ኛ ስትሆን ኢትዮጵያውያኑ አየል ልቅና እና ሀቨን ሀይሉ 4ኛ እና 5ኛ ሆነው አጠናቀዋል።
ፈለቀ ደምሴ