ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በባርሴሎና ክብረ-ወሰን ጭምር በማሻሻል አሸነፉ።

▪️ኢትዮጵያዊያኑ እጅጋየሁ ታየ እና በሪሁ አረጋዊ በ cursa dels nassons  ባርሴሎና የተካሄደውን የ 5 ኪሎሜትር የሩጫ ውድድር በሁለቱም ፆታ የአለምን ሪከርድ ጭምር በማሻሻል አመርቂ ውጤትን አስመዝግበዋል።

▪️የ21 አመቷ እጅጋየሁ ታየ የአመቱ መጀመሪያ አካባቢ በ3000 ሜትር 8:19:52 መግባቷ ይታወሳል። ዘንድሮም በ5000 ሜትሩ 2ተኛ ፈጣኗ ሴት ተብላም ነበር። እጅጋየሁ በሩጫ ህይወቷ የጎዳና ላይ ሩጫ ስትሮጥ ይህ ለ2ኛ ጊዜዋ ብቻ ቢሆንም በባርሴሎና ሪከርድ በማሻሻል ጭምር 14:19 በመግባት ድልን መጎናፀፍ ችላለች። ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ግን በዜግነት ስዊድናዊ የሆነችው ምዕራፍ ባህታ 2ኛ ስትሆን ስፔናዊቷ አትሌት ካርላ ዶሚኒጌዝ 3ኛ ሆና ውድድሯን አጠናቃለች።

▪️የ 20 አመቱ በሪሁ አረጋዊ ባሳለፍነው ወር በኬንያዊው ጆሺዋ ቼፕቲጊ የተያዘውን የአለም ሻምፒዮና ሪከርድ ለማሻሻል ከጫፍ ደርሶ ነበር። የዳይመንድ ሊጉ አሸናፊ በሪሁ አረጋዊ ውድድሩን ለማጠናቀቅ 12:49 የፈጀበት ሲሆን የቼፕቲጊ ተይዞ የነበረውን ሪከርድ በ 2 ሰከንድ አሻሽሎታል።ኬንያዊው ፒተር ማሩ 2ኛ እንዲሁም ኔዘርላንዳዊው ማይክ ፎፐን 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

ፈለቀ ደምሴ

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.