4 ጎሎች የተቆጠሩበት የቼልሲ እና ሊቨርፑል ፍጥጫ።

▪️በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ትላንት በተካሄደ ተጠባቂ ጨዋታ ቼልሲን ከ ሊቨርፑል ጋር ያገናኘ ነበር። ሁለቱም ቡድኖች ከመሪው ማንቸስተር ሲቲ ጋር ያላቸውን ነጥብ ለማጥበብ ወደሜዳ ገብተዋል። ቼልሲ ግዙፉ አጥቂያቸውን ሮሜሉ ሉካኩን ሰሞኑን በሰጠው አወዛጋቢ አስተያየት ቶማስ ቱኸል በቡድኑ ላለማካተት ወስኖ አላሳለፈውም።ከጨዋታው በፊት ‘ለምን’ ብሎ ሲጠይቃቸው ብዙ ድምፆች እንዲነሱ አድርጎል እኛ ደግሞ ዝግጅት ላይ ነን ትልቅ ጨዋታ ነው ያለብን ስለዚህ ዝግጅታችን ላይ ተፅእኖ እንዳይፈጥር በማሰብ ነው ያላካተትኩት ንግግርም አድርገናል ሁለት ጊዜ አናግሬዋለሁ ስለዚህ ዝግጅታችንን ላይ እንቅፋት እንዳይሆን ብዬ ነው እንዲካተት ያላደረኩት ብለዋል።

ሊቨርፑል በበኩሉ አሰልጣኙን የርገን ክሎፕን እንዲሁም በረኛው አሊሰን ቤከር ፣ አጥቂው ሮቤርቶ ፊርሚንሆን እና ተከላካዩን ጆኤል ማቲፕን በኮቪድ/ኦሚክሮን ቫይረስ ምክንያት ግልጋሎታቸውን ሳያገኝ ነው ወደሜዳ የገባው።ጨዋታው በሁለቱም ቡድኖች ለማሸነፍ እና 3 ነጥቧን የግላቸው ለማድረግ ነበር የገቡት 9ኛው ደቂቃ ላይ ሴኔጋላዊው ሳድዮ ማኔ የብሄራዊ ቡድን ጓደኛውን ኤዱዋርድ ሜንዲን በማታለል የመጀመሪያውን ጎል አስቆጠረ። ሳድዮ ማኔ ባሳለፍነው አመት ጀምሮ ስታምፎርድ ብሪጅ ላይ ብዙ ጎል ያስቆጠረ ተጫዋች ሆኗል። የትላንቱን ጨምሮ 3 ጎሎችን ሰማያዊዎቹ ላይ ማስቆጠር ችሏል።

ከዛም ከ 17 ደቂቃዎች በኋላ ሌላው አፍሪካዊ ሞሀመድ ሳላህ የግል ብቃቱን ተጠቅሞ 2ኛውን ጎል ለቡድኑ ማስቆጠር ችሏል።

ይህ ጎል ቢገባም ቼልሲዎች ግን ተስፋ አልቆረጡም ማርኮስ አሎንሶ ያሻማውን ማዕዘን ምት በረኛው ኬልኸር አውጥቶ ነበር ግን 16:50 ላይ በተጠንቀቅ ሲጠብቅ የነበረው ክሮሻዊው ማትዮ ኮቫሲች አስደናቂ ግብ 42 ደቂቃ ላይ አስቆጥሮ ቼልሲዎችን ማነቃቃት ቻለ።

ከ 3 ደቂቃዎች በኋላ አሜሪካዊው ክሪስታን ፑልሲች ከ ንጎሎ ካንቴ የተሻገረለትን ኳስ ጥሩ አጨራረስ ታክሎበት ቡድኑ ለዕረፍት አቻ ሆኖ እንዲወጣ አስችሏል። ከእረፍት መልስ ምንም ቅያሪ ያላደረጉት ሁለቱም ቡድኖች ጥሩ ፉክክር አድርገዋል ሊቩርፑል በሳድዮ ማኔ እና ሞሀመድ ሳላህ አማካኝነት በተደጋጋሚ ሙከራዎችን ቢያደርጉም ኤዱ ሜንዲ ግን ቼልሲዎች መታደግ ችሏል ቼልሲዎችም በሜሰን ማውንት እና ክሪስታን ፑልሲች አማካኝነት ሙከራዎችን አድርገው ጨዋታውን ለማሸነፍ ጥረት ቢያደርጉም ሳይሳካ ቀርቶ ጨዋታው 2 አቻ ተጠናቋል።

ማንቸስተር ሲቲ በውጤቱ የተጠቀመ ብቸኛው ክለብ ነው ምክንያቱ ደግሞ ከተከታዩ ቼልሲ ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት ወደ 10 መስፋቱ ነው። ሊቨርፑል 1 ቀሪ ጨዋታ እያለው በ 42 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

▪️በሊቨርፑል በኩል ጎል አስቆጣሪዎቹን ሳድዮ ማኔ እና ሞሀመድ ሳላህን እንዲሁም አማካዩ ናቢ ኪዬታን የፊታችን ጥር 1 በሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ምክንያት የሚያጣ በመሆኑ ለመጪው ጨዋታዎች ሊቸገር እንደሚችል ሲገመት ቼልሲዎች በአንፃሩ ኤዱ ሜንዲ ከትላንቱ ጨዋታ በኋላ ወደ ሴኔጋል ይሸኙታል። ስፔናዊው ኬፓ አሪዛባላጋ ቦታውንም እንደሚሸፍን ይጠበቃል።

ሚካኤል ደጀኔ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.