ምባፔ ስለወደፊቱ ተናግሯል።

▪️ኪሊያን ምባፔ ከ ሲ ኤን ኤን ጋር በነበረው ቆይታ በጥር የዝውውር መስኮቱ ሪያል ማድሪድን እንደማይቀላቀል አስታውቋል። “በጥር የማይታሰብ ነው አይሆንም እዚሁ ነኝ” ሲል ነው የተደመጠው።
ሙሉ ስሙ ኪሊያን ምባፔ ሎቲን ሲሆን 23 አመቱ ነው። የብራዚሉ ፔሌን በመከተል በእድሜ ትንሽ ሆኖ አለም ዋንጫን ያነሳ ተጫዋች ነው። በ19 አመቱ ሩሲያ ያወጋጀችውን የአለም ዋንጫ ከሀገሩ ፈረንሳይ ጋር በመሆን ማንሳቱ አይዘነጋም።

▪️ፓሪስ ሴንት ጄርሜ ውስጥ ነው ያለሁት እዚ በጣም ደስተኛ ነኝ 100 በ 100 ይህን የውድድር አመት የ ፒ ኤስ ጂ ተጫዋች ሆኜ ነው ምጨርሰው የተቻለኝን ሁሉ እዚ እስካለሁ ድረስ ለክለቡ አስተዋፆኦዬን አበረክታለሁ ብሏል። ጋዜጠኛውም በሰኔ ወር ኮንትራትህ ያበቃል ያኔስ የሚል ጥያቄ አንስቶለት ነበር ምፓፔም እሱን ለማውራት ጊዜው አሁን እንዳልሆነ እና ጭንቅላቴ ውስጥ አሁን ማስበው የሊግ 1 እና የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ማሳካት ነው። አዎ ከ ሪያል ማድሪድ ጋር ተፋጠናል ግን እኔ ከ ቡድን አጋሮቼጋር በመሆን ማድሪድን አሸንፈን ሩብ ፍፃሜውን እንደምንቀላቀል ተስፋ አደርጋለሁ ሲል መልሷል። ግን ባለፈው አመት ክለቡን መልቀቅ ፈልገህ አልወጣህም ይቆጭሀል ወይ? ብሎ ጋዜጠኛው የመጨረሻ ጥያቄ አቅርቦለት  ማንም ሚቆጨው ነገር እንደሌለ እና አላማ እና ሀሳቡን በግልፆ ለ ፓሪስ ሴንት ጄርሜ አመራሮች እንዳስታወቀ ተናግራል። ከአውሮፓ ዋንጫ በፊት ክለቡን መልቀቅ እንደምፈልግ እና ተተኪ ተጫዋች እንዲያመጡ ጠቁሜ ነበር አላማዬ በፍቅር መለያየት ነው በነፃ መሄድም አልፈለኩም ነበር ክለቡ ግን ሊለቀኝ ፈቃደኛ አልነበረም ይህ ክለብ በ 18 አመቴ ነው የተቀበለኝ 4 አመት አሳልፌበታለሁ እና ምስጋና ቢስ መሆን አልፈልግም። ያልተሳካ ዝውውር ራሱ ለክለቡ ያለኝን ክብር አይቀንሰውም እስከ መጨረሻ ቀኔ ድረስ አሁንም ለክለቡ የቻልኩትን አደርጋለሁ ሲል መልስ ሰጥቷል።

▪️በመጨረሻም የዘንድሮ የባሎንዶር ሽልማት በፓሪስ ቴያትር ዴ ቻትሌት ሲካሄድ ከተገኙት እንግዶች መካከል አንዱ የሆሊውድ ፊልም ሚተውነው እና በአጭር ጊዜእውቅናን ማትረፍ የቻለው  እና ማርቭል ስቱዲዮ ሚያዘጋጀው ስፓይደር-ማን ፊልም በመተወን ሚታወቀው ቶም ሆላንድ አንዱ ነው። እናም ቶም የቶተንሀም ደጋፊ እንደሆነ ይታወቃል እና ምባፔን ወደ ቶተንሀም አትመጣም ወይ ሲል ጠይቆት ነበር እና የሲኤን ኤን ስፖርት ጋዜጠኛዋም ይህን ጥያቄ ደግማ ወደ ሰሜን ለንደን የመሄድ ሀሳብ የለህም ወይ ብላ ለምባፔ አቅርባለት ነበር። እሱም ከሳቀ በኋላ ጓደኞቼ እዛ አሉ እነ ንዶምቤሌ እነ ሁጎ ሎሪስ አሁን ደግሞ ኮንቴን ስለሾሙ ጥሩ ይንቀሳቀሳሉ ብዬ እገምታለሁ እኔ ግን በእግርኳስ ህይወት ውስጥ ምን እንደሚፈጠር ባይታወቅም ወደ እዛ ማቀና ግን አይመስለኝም ሲል የመጨረሻ አስተያየቱን ሰጥቷል።

ሚካኤል ደጀኔ።

Michael dejene

Michael dejene Bsc in computer science Born in october 12,1998 Age 23 Editor of ethiopianssport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.